Vehicle purchase
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ የቢሮ መገልገያዎችን እና ተሽከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር EliG/05/2026
ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ከዚህ በታች የተገለፁ የቢሮ መገልገያዎችን እና ተሸከርካሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
ሎት |
አይነት |
መለያ |
|
1 |
ሎት 1 |
የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎች |
BYD Seagull, BYD Yuan Up |
|
2 |
ሎት 2 |
ኮምፒውተሮች |
ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች |
በጨረታው ለመሳተፍ፡-
1. ተጫራቾች ከላይ ከተገለፁት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ በሁሉም ወይም በተናጠል መወዳደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች በመስኩ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፤ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የግብር ግዴታቸውን የተወጡ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሚወዳደሩበት ለሎት 1 የብር 50,000(ሀምሳ ሺህ) እና ለሎት 2 ደግሞ የብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር) በኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ስም በሲፒኦ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ጋር አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዘወትር በስራ ሰዓት መስቀል ፍላወር በሚገኘው የኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መስሪያ ቤት “ሆም ኦፍ ሚሲዮንስ” ህንፃ 5ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ ስለጨረታው የሚገልፀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እስከ ነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በዚሁ ነሀሴ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ በኩባንያው የስልጠና አዳርሽ 8ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።
7. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 470 2077 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
8. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው/
አድራሻ፡- ኢትዮ ላይፍ ኤንድ ጀነራል ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መ/ቤት መስቀል ፍላወር ሆም ኦፍ ሚሊዮንስ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ
ስልክ 011 470 2077 / 011 557 0606
Tender details
- Deadline: 2026-08-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-08-17 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethio Life and General Insurance S.C
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T13:01:59.000Z