Strategy, business and feasibility studies
ገነተ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 542 የሆኑትን ሕንፃዎች እና በድርጅቱ ስም የሚገኙትን ንብረት በገበያ ዋጋ እንዲጠናለት እና የንብረቶች አቻ ግምቱን በባለሞያ ለማስጠናት ይፈልጋል
Description
የሕንፃ እና ቋሚ ንብረት የዋጋ አቻ ግምት ትመና
የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ገነተ ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 እና በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር 542 የሆኑትን ሕንፃዎች እና በድርጅቱ ስም የሚገኙትን ንብረት በገበያ ዋጋ እንዲጠናለት እና የንብረቶች አቻ ግምቱን በባለሞያ ለማስጠናት ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ የግምት ስራ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው እና የስራ ፍቃዱ በገቢዎች ሚኒስቴር ጭምር ዕውቅናና ተቀባይነት ያለው ድርጅት በጨረታው እንዲሳተፍ እና በቴክኒካል እና በፋይናንሺያል ውጤቱ የተሻለ ተወዳዳሪን መርጠን የምናሰራ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው ሁኔታ፣ ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
1. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት 7 የሥራ የ ቀናት ውስጥ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ቢሮ 1ኛ ፎቅ በአካል ተገኝተው የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ፕሮፖዛላቸውን ማስገባት ይችላሉ።
2. ሌሎች ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ፣ ወረዳ 03 የቤት ቁጥር 755 በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ፋይናንስና አስተዳደር ቢሮ 1ኛ ፎቅ ውስጥ በሚገኝ የጨረታ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ዘወትር ከ3፡00 እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት ይችላሉ።
4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ኛ የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ከላይ በተጠቀሰው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 1ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ 8ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
5. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0911 404 541 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡ አፍሪካ ጎዳና ቦሌ ጃፓን ትራፊክ መብራት አጠገብ፣ኢትዮ ሴራሚክ ፊትለፊት የቀድሞ ኖቪስ ሱፐርማርኬት የነበረበት ገነተ ህንጻ 1ኛ ፎቅ
Tender details
- Deadline: 2026-08-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ኛ የስራ ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-18 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8ኛ የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Genete Limat Pvt.Ltd.Co.
- Buyer address: አ.አ ክ/ከተማ ቂርቆስ ወረዳ 2 ቤት ቁጥር 802-14
- Published on: Reporter (Aug 09, 2026)
- Posted at: 2026-08-10T13:39:32.000Z