Products and Services

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት (ገዢው አካል) በክልሉ ለሚያስፈልግ የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የእህል፣ የጥራጥሬ፣ የምግብ ዘይት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን (NFI Kits) ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ (National Competitive Bidding - NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ክፍል 1: የጨረታ ጥሪ ማስታወቂያ

(Invitation for Bids - IFB)

ለተከበራችሁ ህጋዊ አቅራቢዎች በሙሉ!

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት (ገዢው አካል) በክልሉ ለሚያስፈልግ የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት የሚውሉ የእህል፣ የጥራጥሬ፣ የምግብ ዘይት እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን (NFI Kits) ህጋዊና ብቃት ካላቸው አቅራቢዎች በግልፅ ጨረታ (National Competitive Bidding - NCB) አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጨራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡

  • በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና የቫት (VAT) ምዝገባ ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
  • የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በአቅራቢዎች ዝርዝር (Supplier List) ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የ2017/2018 ግብር ከፋይነታቸውን የሚያረጋግጥ የነፃነት ደብዳቤ (Tax Clearance) ማቅረብ የሚችሉ።
  • ተጨራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። የጨረታው ሰነድ ስርዝ ድልዝ ያለው ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
  • የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በእለቱ ከቀኑ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  • ገዢው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0915 102 271 እና 0913 438 803

የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-27 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Hareri
  • Publishing entity: የሀረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግሥት አደጋ መከላከል እና የምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T07:56:06.000Z
← Back to all tenders