Equipment and Accessories

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት አመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ለመጀመረያ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2019 በጀት አመት ለወረዳው አገልግሎት የሚውሉ

  • ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያ፣  
  • ሎት 2 ኤሌክትሮኒክስ፣
  • ሎት 3 የፅዳት እቃዎች፣
  • ሎት4 የስፓርት ትጥቅና ቁሳቁስ፣
  • ሎት 5 የውሃ እቃዎችና መገጣጠሚያ፣
  • ሎት 6 የተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ እቃዎች፣
  • ሎት 7 የእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ፣
  • ሎት 8 ቋሚ አላቂ እቃዎች፣
  • ሎት 9 ደንብ ልብስ፣
  • ሎት 10 ቋሚ እቃዎችና መሰል (ፈሪኒቸር ውጤቶች)፣
  • ሎት 11 ኬሚካል አፓራተስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈረቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ

3. የግብር ከፈይ መልያ ቁጥር (ቲን ነበር) ያላቸው

4. የድርጅት ህጋዊ ማህተም ያለው (ያላት)

5. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዚያበላይ ከሆነ የተጨማር እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገበና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል (የምትችል)

6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢኒ ቦንድ) ለፅህፈት መሳርያ 35000(ሰላሳ አምስት ሺ ብር)፤ ለኤሌኪትሮኒክስ 60,000 (ስልሳ ሺ ብር)፤ ለፅዳት እቃዎች 6000 ብር (ስድስት ሺ ብር)፤ ደንብ ልብስ 30,000 ብር (ሰላሳ ሺ ብር) ለስፖርት ትጥቅና ቁሳቁስ 25,000 ብር (ሀያ አምስት ሺብር)፤ ለቋሚ አላቂ እቃዎች 15,000 ብር (አስራምስት ሺህ)፤ ለውሃ እቃና መገጣጠሚያ እቃዎች 30,000 ብር (ሰላሳ ሺህ)፤ ለተሽከርካሪ ጎማና መለዋወጫ 16000 ብር (አስራ ስድሰት ሺህ)፤ ለእንስሳት መድሀኒትና መገልገያ ቋሚ አላቂ እቃዎች 10,000ብር (አስር ሺህ)፤ ለኬሚካል አፓራተስ 10,000 ብር (አስር ሺህ)፤ ለቋሚ እቃዎችና መስል 60,000ብር (ሲልሳ ሺህ ብር)የጨረታ ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብደረሰኝ ወይም ከሚታወቁ ባንኮች የሚሰጥ ሲ/ፒ/ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ከመጫረቻ ሰነዶችጋር ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች የሚሰጡትን የጨረታዋጋ የጨረታ ሰነዱ በሚጠይቀው መሰረት በማዘጋጀትና በጥንቃቄ በመሙላት በታሸገፓስታ ኢንቮልቭ በማደረግ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡደን ቢሮ ቁጥር 3 ለዚሁተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል። ጨረታው በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ላይ ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።

8. የእቃዎቹን አይነት ዝርዝር መግለጫ (እስፌስፈኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ትችላላችሁ። የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500 ብር (አምስት መቶ ብር) በመክፈል በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በፋይናስ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በከፊል (መሉ በሙሉ) ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

10. ጨረታው የሚከፈትበትቀን ቅዳሜና እሁድ እንዲሁም ብሄራዊ በአላት ላይ የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት መሆኑ ይታወቃል።

11. የጨረታው ተሳታፊዎች ፓስታ ላይም ሆነ ዋጋ መሙያው ላይ ማህተም ማደርግ ይኖረባቸዋል።

12. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት በጠቅላላው ድምር ዝቅተኛ ዋጋ የሞላውነው።

13. የጨረታ ጸንቶ መቆያ ግዜው 45ቀን መሆኑን እናሳውቃለን።

14. ተጫራቾች ካሁን በፊት ተጫርተው ህጋዊ እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን አለባቸው። ለዚህም ማረጋገጫ ከሰሩበት ወይም ካሁን በፊት ካቀረቡበት ተቋም የመልካምስራ አፈፃፅም ማምጣት ይኖርባቸዋል።

15. አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥቡድን ቢሮ ቁጥር 3 ድርስ ማቅረብ ይኖርበታል።

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ግዥቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0111190280 ማግኘት ይችላሉ።

አድራሻ፡- ከአ/አባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 ኪ/ሜ ከደ/ብርሃን 83 ኪ/ሜ እንገኛለን።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን በእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት)
  • Bid opening: 2026-08-25 10:30
  • Bid opening (note): ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆጠር እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት)
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Ensaro Woreda Finance and Economic Development Bureau
  • Buyer address: ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 ኪ.ሜ ከደብረ ብርሃን በስተ ምዕራብ 83 ኪ.ሜ የእንሳሮ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዢና ንብረት አስተዳደር ቡድን
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 10, 2026)
  • Posted at: 2026-08-11T08:48:13.000Z
← Back to all tenders