Catering and Cafeteria Services

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር የካ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት 001/2019

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት የግዥ ቡድን አንደኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የ2019 በጀት ዓመት

  • ሎት 1 መስተንግዶ፣ ዉሃ፣ ቆሎና ኩኪስ፣
  • ሎት 2 ዲኮር፣ ሞንታርቦና ድንኳን ኪራይ፣
  • ሎት 3 የተለያዩ የደንብ ልብሶች፣
  • ሎት 4 የተለያዩ ህትመቶች፣
  • ሎት 5 የተለያዩ የፕሪንተር ጥገናዎችና እቃዎች፣
  • ሎት 6 የመኪና ጌጣጌጥ፣
  • ሎት 7 እስቴሽነሪ ግዥ፣
  • ሎት 8 የተለያዩ የፕሪንተር ቀለሞች፣
  • ሎት 9 ትርጉም፣
  • ሎት 10 የጽዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት 11 የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸርና ጠረጴዛ ጥገናዎች፣
  • ሎት 12 የጎማ ግዥዎች፣
  • ሎት 13 የተለያዩ የግብርና ግብአቶች፣
  • ሎት14 የመኪና ኪራይ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት እንድትጫረቱ ይጋብዛል፤

1. ተጫራቾች በሚሳተፉበት የግዥ አይነት በዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀትና ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች ናሙና እንዲያቀርቡ የተጠየቁባቸውን እቃዎች ሰነዳቸውን ሲያስገቡ አብረው የሚወዳደሩበትን ናሙና የማስገባት ግዴታ አለባቸው።

4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ከሚመለከተው የገቢ ግብር ባለስልጣን ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ሎት 1 30,000 ብር፣ ሎት 2 ብር 30,000፣ በሎት 3 30,000 ብር፣ ሎት 4 30,000 ብር፣ ሎት 5 10,000 ብር፣ ሎት 6. 25,000 ብር፣ ሎት 7. 20,000 ብር፣ ሎት 8. 30,000 ብር ሎት 9. 10000 ብር፣ ሎት 10 30,000 ብር፣ ሎት 11. 15,000 ብር፣ ሎት 12. 25,000 ብር ፣ሎት 13. 30,000 ብር፣ ሎት 14. 30,000 ብር የካ ክፍለ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በየሎቱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣

7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በሚገባ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ፋይናሺያል ዶክመንት በሁለት ኮፒ እና ቴክኒካል ሁለት ኮፒ ሰነድ ለየብቻ ኦርጅናል እና ኮፒውን መሆኑን በመፃፍ በተለያየ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ዋና እና ኮፒ መሆኑን ገላጭ ፅሑፍ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤

8. የጨረታ ሰነድ እስከ 10 ቀን ብቻ ተሽጦ የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ እለት 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የመንግስት ግዥ ቡድን ቢሮ ውስጥ ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ስርዝ ድልዝ የሌለበትና ቫትን ያካተተ መሆኑንና አለመሆኑን ካልተገለፀ የቀረበው ዋጋ ቫትን እንዳካተት ተደርጐ ይወስዳል።

10. ጨረታ ሲያሸንፉ 10% CPO ያሸነፉትን እቃዎች ዉል ማስከበሪያ ማስያዝ አለባቸዉ።

11. ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ያላሟላ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- መገናኛ ማራቶን ሕንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ስልክ 011 810 7894

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ሥራዎች ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-25
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-25 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Sub City Design & Construction Works Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 13, 2026)
  • Posted at: 2026-08-13T08:49:21.000Z
← Back to all tenders