Raw materials
የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የምርት ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡_ አቤሜኢ/ሰቼማ/ግጨ/2019/01
የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ የምርት ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፣ አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ቅጂውን፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣የተጨማረ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዚክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ-ዓርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰዓት 7፡00-11፡00 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ሳይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8:15 ሳይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 1ኛ ወለል ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ውስጥ ይከፈታል።
5. ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
6, ኢንዱስትሪው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
7. ቲክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ሆኖ በኤንቨሎፕ አሽጎ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት፤
አድራሻ፡- ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ሸገር ከተማ የቀድሞ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASICO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፦ 0114340409/0114350608
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ አቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ሳይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 14:15
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ሳይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡15 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Akaki Basic Metals Industry
- Buyer address: ከአአ ወደ ደ/ዘይት መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል
- Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T08:17:25.000Z