Equipment and Accessories
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሰርቨር አገልግሎት የሚውል UPS በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Addis Ababa
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሰርቨር አገልግሎት የሚውል UPS በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፡-
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሳብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ሰነዱ ላይ ለተጠቀሱት ዕቃዎች ዋጋ ዝርዝር በመሙላት በአገልገሎቱ ዋና መ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ቀኑ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጫራቾች ዋጋ በግልጽ የሚነበብና ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን ይኖርበታል። ስርዝ ድልዝ ያለበት የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ በ4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት /Refugees & Returnees Service/ በሚል የተዘጋጀ የባንክ ማዘዣ /CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሁለት ሰነዶች ማለትም ቴክኒካል ፕሮፖዛል እና ፋይናንሽያል ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለየብቻ በማሸግ አገልግሎት መስሪያ ቤቱ በሚያዘጋጀውየጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ጥሪ በደረሰው በ05 /አምስት/ ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ የሥራ ውል መፈረም አለበት።
- አሸናፊው ጥሪ በደረሰው በአምስት ቀናት ውስጥ በአገልግሎቱ ዋና መ/ቤት ቀርቦ ውል ካልፈረመ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመ/ቤቱ ገቢ ይሆናል።
- የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
የእንቁላል ፋብሪካ አደባባይን ሳይሻገሩ
ከፌደራል ፖሊስ ክበብ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር፡- 09-97-23-66-31/0943-01-29-44
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-08-26
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-26 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Refugee and Returnee Service
- Buyer address: ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር ያህል ገባ ብሎ ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T09:10:59.000Z