Equipment and Accessories

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የቢሮውን ተሽከርካሪዎች ስምሪት አና ክትትል ለማድረግ ያመች ዘንድ በተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም ጅ.ፒ.ኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ከመፈፀም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የቢሮውን ተሽከርካሪዎች ስምሪት አና ክትትል ለማድረግ ያመች ዘንድ በተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም ጅ.ፒ.ኤስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ከመፈፀም ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያካቸው።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርብ።

3. ከላይ በተራ. ቁ 1-2 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።

4. የሚገዛው ዕቃ ጠቅላላ ዋጋ ከ 200,000.00/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።

5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ ብር 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ካይ ያተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላላ ዋጋ ከ 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር /መብለጥ የለበትም።

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጊዜያዊነት በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን በ 8:30 ሰዓት ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።

8. ለህክምና መሳሪያ ግዥ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ እንዲሁም የቴክኒካል ዶክመንት ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።

10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።

11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸዉን ዕቃዎች በራሱ ወጭ አብክመ ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።

12. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15/አስራ አምስት/ ቀናት እስከ 11፡30 ድረስ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1000.00 / አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከቢሮው ገንዘብ ያዥ ባለሙያዎች እጅ በአካል ቀርበው መግዛት ይቻላል።

13. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

14. ስለጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ስልክ ቁጥር፡- 058-222-1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

የአብክመ ጤና ቢሮ
ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-08-31
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ 8:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-31 15:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ 9:00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Health Bureau
  • Bid bond: 2% ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያው ጠቅላላ ዋጋ ከ 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር /መብለጥ የለበትም
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሰነድ ብር 1000.00 ( አንድ ሺህ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
  • Posted at: 2026-08-15T09:20:09.000Z
← Back to all tenders