Equipment and Accessories
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣብያ የ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/17314/2018 ዓ.ም
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣብያ የ2019 በጀት ዓመት የጨረታ ቁጥር 001/2019 ዓ.ም
|
1. የቢሮ እቃዎች |
ሎት .1 4,500.00 ብር |
|
2. የጽዳት እቃዎች |
ሎት. 2 7,000.00 ብር |
|
3. የደንብ ልብስ |
ሎት.3 10,000.00 ብር |
|
4. ቋሚ እቃዎች |
ሎት.4 18,000.00 ብር |
|
5. ሕትመት ውጤቶች |
ሎት.5 10,500.00 ብር |
|
6. የሰው መድኃኒት |
ሎት.6 25,000.00 ብር |
|
7. የህክምና መሳሪያዎች |
ሎት.7 25,000.00 ብር |
|
8. ለቁሳቁስ ተገጣጣሚ መግዣ |
ሎት.8 2,500.00 ብር |
|
9. ለህንጻ ቁሳቁስን እድሳት |
ሎት. 9 20,000.00 ብር |
|
10. ደንብ ልብስ ስፌት |
ሎት.10 500.00 |
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡
1. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ።
2. የንግድ ምዝገባ ::
3. የግብር ከሊራንስ።
4. የአቅራቢነት ሊስት መመዝገባቸውን /በዌብ ሳይት ይረጋገጣል ።
5. የVAT ተመዝጋቢነት መረጃ።
6. የጥቃቅንና አነስተኛ በሚያመርቱት ምርት የሚገልፀ ደብዳቤ ማፃፍ ይኖርባቸዋል።
7. ለጥገና ስራ የሚጫረቱ በሌላ ድርጅት መስራታችሁን የሚገልጽ የመልካም አፈጻጸም ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል።
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ብቻ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ 300( ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከ ጤና ጣብያው ረዳት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 49 ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
9. ተጫራች ከታወቀ ባንከ የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ስር የተጻፈውን ማቅረብ ይኖርበታል ።
10. የጨረታ ማስከበሪያ እና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅን እና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበት የንግድ ስራ መስክ /ዘርፍ የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ፡፡
11. ጨረታው ጸንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ60 ቀናት ብቻ ነው።
12. የጨረታ አሸናፊዎች ማሸነፋቸውን የሚገለጽ ደብዳቤ የሚደርሳቸው ሲሆን ውል ማስከበሪያ ለአሸነፈበት ዋጋ 10% CPO ማስያዝ ግዴታ አለበት። እንዲሁም ተጫራቹ እቃዎቹን በራሱ ትራንስፖርት እቃ ግምጃ ቤታችን ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት 3፡00‐5.30 እና 7፡30-9፡30 ድረስ አቅርቦ ማስረከብ አለበት::
13. ክፍያ የሚፈጸመው ለሚያቀርቡት እቃ ሙሉ በሙሉ በናሙናው መሰረት ጥራቱ ሲረጋገጥና ከንብረት ክፍል በሞዴል 19 ገቢ ሲሆን ብቻ ነው።
14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዋናውን እና ኮፒውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ሙሉ ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በ10 ኛው ቀን ልክ 11፡30 ሰዓት ሚያበቃ ሲሆን በ11ኛው ቀን በ 3፡30 ታሽጎ በዛው ቀን 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል::
15. ጤና ጣቢያው የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
16. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የአንድ ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
17. ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
18. ለቋሚ እቃዎች በሚቀርበው ስፔስፊኬሽን ሰረት ሆኖ በተጨማሪ ፎቶ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
19. ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ከፊትና ከዋላ ማህተም የድርጅቱን ስምና ፊርማ ሳያደርግ ዋጋ ሳይሞላ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ሰነዱ ለውድድር አይቀርብም ።
20. የጨረታ አሸናፊዎች ወይም ድርጅት ማሸነፉ እንደተረጋገጠ በተሰጠው የጊዜ ገደብ ቀርቦ ውል መፈጸም አለበት ።
21. ተጫራቾች በጨረታው ላይ በተጫራች የሚሞሉ ክፍሎችን እና ዋጋ የሚሞላው ክፍል 4 እና ክፍል 6 የመሙላት ግዴታ አለባቸው። በተጨማሪም CPO የተሰላው ከተፈቀደለት በጀት 0.5% ነው።
አድራሻ፡- አጠና ተራ ሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ
ለበለጠ መረጃ :- 0112-73-86-34 / 011-273-87-17
አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የሎሚ ሜዳ ጤና ጣብያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-27
- Bid closing time: 09:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-08-27 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lomi Meda Health Center
- Buyer address: ኮልፌ አጠና ተራ ወደ ሎሚ ሜዳ በሚወስደው ታክሲ መውረጃ ፊት ለፊት ባለው ሎሚ ሜዳ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 15, 2026)
- Posted at: 2026-08-15T10:38:46.000Z