Vehicles Purchase
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራ ዩኒዩን ኃ/የተወሰነ ለዩንዩኑ ምርት እና ግብአት ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውል ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 (አራት መቶ) የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሰት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳዳር በሰቆጣ ከተማ የሚገኘው የዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ስራ ማህበራ ዩኒዩን ኃ/የተወሰነ ለዩንዩኑ ምርት እና ግብአት ለማጓጓዝ አገልግሎት የሚውል ሲኖ ካሶኒ 2025 ሞዴል ባለ 400 (አራት መቶ የፈረስ ጉልበት የጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በመሆኑም የሚከተሉትን የተገለፁት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታዉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋበዛል ::
1. በዘመኑ የ2018 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለቸዉና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና (የምትችል) ከሚገዛዉ የጭነት ተሽከርካሪ አገልግሎት ጋር የተዛመደ ንግድ ስራ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት(Value Added Tax Certificate) ተመዝጋቢ ከሆነ የግብር ከፋይነት ምስክር ወረቀት(Tax Payer ldentificain Number) እንዲሁም ሌሎች ለጨረታው የሚጠቀሙ ማስረጃዎችን የተገናዘበ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል (የምትችል)
2. ተጨራቾች የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ደንበል ጀርባ/ኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ቢሮ 1ኛ ፎቅ በሚገኘዉ ሪጉላቶሪ ክፍል ብር 250 /ሁለት መቶ ሀምሳ ብር/ ብቻ በመክፍል የጨረታ ሰነድ መግዛት ይኖርባችዋል።
3. የጨረታ ተሳታፊዎች የመሸጫ ዋጋቸውን በሰንጠረዥ በተገለጸዉ ዝርዝር ሁኔታ መሰረት መሙላት አላባቸዉ
4 የጨረታ ዋጋዉ ከመግለፅ በፊት የጨረታ ማስከበሪያ ተጫራቾች በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተፈቀደላቸዉ በታወቁ ባንኮች ዋስትና ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (C.PO) ወይም በጥሬ ገንዘብ ዋናውን የገቢ ደረሰኝ ከማወዳደሪያ ሃሳብ ጋር አብሮ ማስገባት ሲኖርባቸው በጨረታ ሰነዱ ከተቀመጠው ዝርዝር መግለጫ ውጭ መጨመርም ሆነ መቀነስ አይፈቀድም።
5. ሌሎች ተጫራቾች በአቀረቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መሙላት አይቻልም።
6. በጨረታዉ የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙንት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለሳል።
7. የጨረታ ሰነዱን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 10/አስር የስራ ቀናት ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታዉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችው በተገኙበት አዲስ አበባ ከተማ/ቦሌ ደንበል ጀርባ/ ኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን ቢሮ 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ሪጉላቶሪ ክፍል ጨረታው በጋዜጣ ከታወጀበት ጊዜ አንስቶ በ11 አስር አንድኛው ቀን ከጥዋቱ 3፡00 ታሽገው ከጥዋቱ 3፡30 ጨረታው ይከፈታል በጨረታ መክፈቻ ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በጨረታ አከፋፈት ባይገኙም በጨረታ አከፋፈት ስርአቱ ተገዥ ይሆናሉ ፡፡
9. አሽናፊዉ እንደታወቀም አሽናፊዉ ያሸነፈበትን የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ ለዉል ማስከበሪያ በማስያዝ (በ5 አምስት) ቀናት ዉል መያዝ አለበት ይህ ካልሆነ ግን ዩንዩኑ የጨረታ ማስከበሪያዉን 2% መቶ በመዉረስ የራሱን አመራጭ ይወስዳል
10. ተጫራቾች ከጨረታው ጋር በተያየዘ እና ሌሎች ዝርዝር ሁኔታዎች በተዘጋጀዉ የተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተገዥ መሆን አለባቸው
11 ዩንየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ይህም ሲባል ጨረታው በመሰረዙ ተጫራቾች በጨረታው ለመወዳደር ላወጡት ወጭ መ/ቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን መገንዘብ ይኖርባችዋ ፡፡
12. ተጫራቾች ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቦሌ ደንበል ጀርባ የኢትዮጵያ ህብረት ስራ ኮሚሽን አዲስ አበባ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0911720797/0941821789 /093324815/ 0968945900 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋ/ኽ/መስ/ር/ዞን
ዋቢ ሁለገብ የገበሬዎች ህብረት ዩኒየን ኃ/የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-08-28
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 3፡00
- Bid opening: 2026-08-28 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን አንስቶ በ11ኛ ቀን ከጥዋቱ 3፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Wabi Farmers Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 250.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 16, 2026)
- Posted at: 2026-08-17T08:55:49.000Z