Industrial Machinery Provision and Installation

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ልማት ጥናትና ፕሮሞሽን አገልግሎት የሚውሉ 6 ፕሮጀክቶች ፕሮፋይሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠናት/ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ 001/2019

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኢንቨስትመንት ልማት ጥናትና ፕሮሞሽን አገልግሎት የሚውሉ 6 ፕሮጀክቶች ፕሮፋይሎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማስጠናት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ፤-

  • 1, Electronic Waste (E-waste) Recycling plant
  • 2. Dehydrated fruit and vegetable processing plant
  • 3. Production of Biodegradable Packaging Materials
  • 4. Surgical Cotton and Bandage Manufacturing plant
  • 5. Electic Vehicle (EV) Assembly plant
  • 6, Mobile Phone charger manufacturing

ለጥናት ፕሮጀክት ፕሮፋይል የሚያስፈልጉ መስፈርቶች

1. ቀደም ሲል የፕሮጀክት ፕሮፋይል ስራ መስራቱን የሚያስረዳ ማስረጃ የሚያቀርብ

2. ለስራው ተገቢ የሆነ የትምህርት ዝግጅት ማቅረብ የሚችል

3. ስድስቱንም ፕሮጀክት ፕሮፋይሎች ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ በ 3 ወራት ውስጥ አጠናቆ ማቅረብ የሚችል

4. እያንዳንዱን ፕሮጀክት ፕሮፋይል ቢያንስ ከ 25 ገጽ ባላነሰ መንገድ የሚሰራ

5. ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ቢያንስ የአምስት ዓመት የአዝማሚያ ትንተና (trend analysis) መስራት የሚችል

6. ለእያንዳንዱ ፕሮጀክት ስራ በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ ትርጉም ማቅረብ የሚችል

7. ለእያነዳንዱ ፕሮጀክት ፕሮፋይል ኢንሴብሽን ሪፖርት እና የስራ ፕሮፖዛል ማቅረብ የሚችል

ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ በመስኩ ስተሰማራችሁ ግለሰቦች (ድርጅቶች) የሚከተሉትን የመወዳደሪያ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችኋል

1. ተጫራቾች 6 ቱንም ወይም በሚፈልጉት ብዛትና ዓይነት መጠን መወዳደር ይችላሉ፤

2. አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በተገለፀበት ከ 5/አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ 7 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ የሚችል መሆን አለበት፤

3 ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የሚያሟሉ ሁሉ የጨረታ ሰነድ/ዶክሜንቱን ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በግዢ፣ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ድረስ በመቅረብ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፤

4. ተወዳዳሪ ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 3፡59 ሰዓት ድረስ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሠንጋ ተራ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ሠንጋ ተራ ዮቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 802 ግዢ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታን ጨምሮ በዕለቱ ይከፈታል፡፡

6. ኮሚሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል (የመወዳደርያ ዋጋ የተሞላበት ሰነድ) ኦርጅናል እና ኮፒ እንዲሁም ቴክኒካል ዶከመንቶችን (ለጨረታ የተጠየቁ አስፈላጊ የንግድ ፍቃዶችና መረጃዎች ኮፒ) በፖስታ ውስጥ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስገባት አለባቸው፤

8. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ተካፋይ ሆኖ ጨረታው ከተከፈተ በኋላ የተሰጠውን ዋጋ ለማሻሻል፣ ለመለወጥ ወይም ትቼዋለሁ ማለት አይችልም፤

9. ማንኛውም ተጫራች ማጭበርበር ወይንም ሙስናን በተመለከተ በኢትዮጵያ ህጎች የተደነገገውን የሚያከብር መሆን ይገባዋል፤

10. ጨረታውን ለማዛባት ሙከራ የሚያደርግ ተጫራች ከጨረታው እንደሚሰረዝ እና ወደፊትም እንዳይሳተፍ እንደሚታገድ እንዲሁም ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስበት ማወቅ ይኖርበታል፤

ማሳሰቢያ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀናት ከሆነ ጨረታው በቀጣዩ የሥራ ቀን ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል፤

አድራሻ፡- ስደታ ክፍስ ከተማ ሜክሲኮ ሠንጋ ተራ የቤክ ህንፃ 8ኛ ፎቅ ቢሮ ቁፕር 802 በግዢ፤ ንብረት አስተዳደርና ጠቅላላ አገስገሱት ዳይሬክቶሬት

ለበለጠ መረጃ በስ.ቁ.011-5-57-78 46 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-08-28
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00
  • Bid opening: 2026-08-28 12:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Investment Commission
  • Buyer address: ልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 09 ዮቤክ ኮሜርሽያል ሴንተር
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
  • Posted at: 2026-08-18T07:37:55.000Z
← Back to all tenders