Equipment and Accessories
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለጋዝጊብላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በዋግ ኽምራ ዞን የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት ለጋዝጊብላ ወረዳ ሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ እቃዎችን ማለትም
- በምድብ 1 የፕሪንተር ቀለሞች እና የጽሕፈት መሣሪያ
- በምድብ 2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን
- በምድብ 3 የፅዳት እቃዎች
- በምድብ 4 የግንባታ እቃዎች
- በምድብ 5. የመኪና ጎማና ባትሪ
- በምድብ 6 የመኪና እቃዎች
- በምድብ 7 የወንድና የሴት ጫማዎች
- በምድብ 8 የወንድና የሴት ሸሚዞች ካፖርት ጨምሮ
- በምድብ 9 ብትን ጨርቅ
- በምድብ 10 የውሃ እቃዎች
- በምድብ 11 የስፖርት እቃዎች እና
- በምድብ 12 ጣውላና ኮፒስታቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ።
1. በየዘርፉ በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆኑን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው።
3 የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መያዝ አለባቸው።
5. የሚገዙትን እቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች በየምድቡ የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል በጋዝጊብላ ወረዳ ገ/ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት ብቻ መግዛት ይጠበቅባቸዋል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ምድብ ከጠቅላላ ዋጋው (ቫትን ጨምሮ) 1 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ አንድ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ዋናውን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል። በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለሚፈልጉ በፖስታ አሽገው የጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡31 ይታሸግና በዚሁ እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው።
9. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም በፍሉድ የተሰረዘ ካለው ሰነዱ ተቀባይነት የለውም።
10. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ሕግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል።
11. የምድብ 7፤ 8 እና 9 አሸናፊ ውለታ ከመውሰዱ በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለበት።
12. መ/ቤቱ በየምድቡ ያሉት የእቃዎቹ የጨረታ ሰነዶች በሎት ወይም በነጠላ ዋጋ የማወዳደር መብቱ የተጠበቀ ነው።
13. የጨረታው አሸናፊ እቃውን በራሱ ትራንስፖርት ጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ አለበት። ከታዘዘው እስፔስፊኬሽን ውጭ እቃ ቢያቀርብ በራሱ ወጭ እቃውን ወስዶ ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት።
14. ተጫራቾች የእቃ ዋጋ ሲሞሉ እስፔስፊኬሽን የሚያስፈልጋቸውን እቃዎች የእቃውን መለያና እስፔስፊኬሽን መሙላት ይጠበቅባቸዋል ነገር ግን እስፔስፊኬሽን እና መለያ የማይሞላ ተጫራች ሰነዱ ተቀባይነት የለውም።
15. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
16. በጨረታው 1ኛ የወጣው ተጫራች ውል እስኪወስድ ድረስ 1ኛና 2ኛ የወጡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስላቸውም ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ግን አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ።
17. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውለታ ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል።
18. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር (ዝግ ከሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
19. ጽ/ቤቱ እንደ አስፈላጊነቱ የግዥ መጠኑን 20 % ከፍና ዝቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
20. በጨረታው ለመሳተፍ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ ቤት ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 09 21 26 48 53 ወይም 09 21 19 21 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጧቱ 3፡31 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-01 12:00
- Bid opening (note): ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Gazigibela Wereda F/E/D/Bureau
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 17, 2026)
- Posted at: 2026-08-18T07:57:42.000Z