Equipment and Accessories

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ግዥ

  • በሎት 1 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ፣
  •  በሎት 2፡- የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ
  • በሎት 3፡ የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ፣
  • በሎት 4፡- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ፣
  • በሎት 5፡- የደንብ ልብስ ግዥ፣
  •  በሎት 6፡- የሞተር ሳይክል ግዥ
  • በሎት 7 የህትመት አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

  1. ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸው፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
  5. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣
    • ለሎት 1፡- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃ ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ/ ብር
    • ለሎት 2፡- የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃ ግዥ ብር 50,000 ብር ሃምሳ ሺህ/ ብር
    • ለሎት 3፡- የሆቴል መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 50,000 ብር ሃምሳ ሺህ ብር/
    • ለሎት 4፡- የጽህፈት መሳሪያ ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር
    • ለሎት 6፡-የሞተር ሳይክል ግዥ ብር 50,000 ብር/ሃምሳ ሺህ ብር/
    • ለሎት 5፡- የደንብ ልብስ ግዥ ብር 40,000 ብር/አርባ ሺህ ብር/
    • በሎት 7፡- የህትመት አገልግሎት ግዥ 40,000 ብር አርባ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያው ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ገቢ መደረግ አለበት፡፡
  9. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ 15ኛው ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Benchi Sheko Zone Finance Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T07:34:19.000Z
← Back to all tenders