Equipment and Accessories
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Oromia
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሸገር ከተማ አስተዳደር የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ.ም በስሩ ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች
- ቋሚ እቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ፈርኒቸሮች)፣
- አላቂ እቃዎች ማለትም (የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች እና
- የተለያዩ መጠን ያላቸው ጎማዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መወዳደር የሚፈልግ ማንኛም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው::
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO) ብቻ 100,000(አንድ መቶ ሺህ ብር ብቻ) በክፍለ ከተማችን ውስጥ ባሉት ባንኮች በተመሰከረ (CPO) ብቻ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ በትክክል በመሙላት በታሸገ ፖስታ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በስንቄ ባንክ አካውንት ቁጥር 1064628071215 የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በማለት ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይንም ቅዳሜ እና እሁድ ቀን ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰነዱ በጨረታ ሳጥን ገብቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ፅ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እየገለጽን ለበለጠ መረጃ የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት እቃ ግዢ ክፍል በአካል ቀርበው መረዳት ይችላሉ፡፡
የሱሉልታ ክፍለ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-09
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ጠዋት እስከ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-09 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ጠዋት እስከ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Sheger City Sululta Sub City Administration FEDB
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
- Posted at: 2026-08-20T07:39:06.000Z