Catering and Cafeteria Services

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የአማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ እና የሚዛን አማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በደ/ምዕ/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በዞኑ ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉል ግዥ

  • በሎት 1- የአማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ፤
  • በሎት 2፡- የሚዛን አማን ሻይ ቡና እና የምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ

በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

  1.  ተጫራቾች በሚጠይቀው ዘርፍ የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸዉና
  2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (tin no) ያላቸዉ፣
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣
  4. የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸዉ፣
  5. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ከግብር ዕዳ ነፃ ስለመሆናቸው ከገቢዎች መ/ቤት ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር፣
    • ለሎት 1 የአማን ሻይ ቡና እና ምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ ብር 40,000 ብር/አርባ ሺህ/ ብር
    • ለሎት 2፡- የሚዛን አማን የሻይ ቡና እና ምግብ መስተንግዶ አገልግሎት ግዥ 40,000 ብር/አርባ ሺህ/ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ፤ በባንክ በተረጋገጠ ጋራንቲ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ ሌተር ኦፍ ክሬዲት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ስለጨረታዉ ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘዉን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከመምሪያዉ የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 100 መግዛት ይችላሉ።
  8.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ሃሳብ ዋናና ኮፒ በማለት ተፈርሞበት በጥንቃቄ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በታሸገ ኤንቨሎፕ በጨረታ ማስታወቂያዉ ከተመለከተዉ የጊዜ ገደብ በፊት የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ፣ የግዥና ንብረት አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 100 ለጨረታዉ በተዘጋጀዉ ሳጥን ዉስጥ ገቢ መደረግ አለበት።
  9. ጨረታዉ ማስታወቂያ በወጣዉ 15ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ታሽጎ በዚያው ቀን በ9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚከፈት ሆኖ የሚታሸግበትም ሆነ የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን ይሆናል።
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0471355629

የቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 15:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15ኛዉ ተከታታይ የስራ ቀን ከቀኑ በ9፡00 ሰዓት
  • Region: South West Ethiopia Region
  • Publishing entity: Benchi Sheko Zone Finance Bureau
  • Bid bond: 40,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
  • Posted at: 2026-08-20T08:32:09.000Z
← Back to all tenders