Medical Equipment and Supplies
በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2019ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 001/2019
በጉለሌ ከ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በ 2019ዓ.ም በጀት ዓመት 1ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ የተለያዩ እቃዎችን ማለትም
- ሎት 1- የተለያዩ መድሃኒቶች፤ የሕክምና ዕቃዎች እና የላብራቶሪ እቃዎች ፣
- ሎት 2- የጽዳት ዕቃዎች ፣
- ሎት 3- የጽህፈት መሳሪያዎች እና ልዩልዩ መሳሪያዎች ፣
- ሎት 4- የደንብ ልብስ ዕቃዎች እና የደንብ ልብስ ስፌት ፣
- ሎት 5- የህትመት ውጤቶችን
- ሎት 6- የቋሚ እቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች
- ሎት 7- ለህንጻ ለቁሳቁስ እና ለተገጣጣሚዎች እድሳትና ጥገና
- ሎት 8- ለሚኒስትሪሚንግ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ማለትም : ኩኪስ፣ ቆሎ፣ ውሃ ለስላሳ መጠጦች እና የተለያዩ ግብዓቶችን ጨምሮ
- ሎት 9- የላዳ እና የፒክ አፕ የትራንስፖርት አገልግሎት
- ሎት 10- ለፕላንት፣ ማሽነሪ እና ለመሳሪያ እድሳት እና ጥገና፣
- ሎት 11- የአልትራ ሳዉንድ ባለሙያ
- ሎት 12-የካፍቴሪያ አገልግሎት ጨረታ ሲሆኑ
ከላይ የተዘረዘሩትን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ከቅላላ ዋጋ ከ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚወዳደሩበት እቃ ለሎት 1- 90,000/ ዘጠና ሺህ ብር ብቻ / ለሎት 2- 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ለሎት 3- 11,000 / አስራ አንድ ሺህ ብር ብቻ /ለሎት/ 4- 11,000/ አስራ አንድ ሺህ ብር ብቻ / ሎት 5- 8000 /ስምንት ሺህ ብር ብቻ / ለሎት 6- 40,000/አርባ ሺህ ብር ብቻ ሎት 7- 45,500/አርባ አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ሎት 8- 1800 /አንድ ሺህ ስምንት መቶ ብር ብቻ/ ሎት 9- 1500 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ብቻ/ ሎት 10- 3800 /ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ብር ብቻ/ሎት 11- 5000 /አምስት ሺህ ብር ብቻ/ሎት 12- 13000 /አስራ ሶስት ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በአዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ስም በማስያዝ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን ሲፒኦ ያላስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል ሲፒኦ ስታስይዙ በሎት ከፋፍላችሁ ከሰነዶቻችሁ ጋር ማቅረብ አለባችሁ።
5. ጥቃቅን እና አነስተኛን በተመለከተ በጨረታ ማስከበሪያ፣ በውል ማስከበሪያና በቅድሚያ ክፍያ ዋስትና ምትክ ከወረዳው የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ ተቀባይነት እንደሚኖረው፣ ለጨረታ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝነት የተቋቋሙበትን ህጋዊ ማስረጃ በማሳየት ያለ ክፍያ በነጻ እንዲያገኙ ይደረጋል። ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነዉ እሴትን ለሚጨመሩ /አምራች ለሆኑ/ ሥራ ዘርፎች ብቻ መሆኑን እናሳዉቃለን። ይሄንን ማስረጃ ካደራጀው አካል በደብዳቤ ተጽፎ ለማያቀርብ ተጫራች የጨረታ ሰነድ በነፃ እንደማይሰጠዉ እናሳዉቃለን።
6. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በራሱ ትራንስፖርት ኣጓጉዞ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ውስጥ ያስረክባል።
7. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በሎት የማይመለስ ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር ብቻ) በመክፈል በጤና ጣቢያው 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 ይህ ማስታወቂያ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር /10/ ተከታታይ የስራ ቀናት በመግዛት የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነድ ላይ በመሙላት ለዚሁ አገልግሎት ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 410 ፊት ለፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ማንኛውም ተጫራች መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ቫትን ጨምሮ ዋጋ መሙላት አለበት፣ የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም እና ፊርማ ማስቀመጥ አለበት የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናል እና ኮፒ በሁለት ፖስታ አሽጎ ማቅረብ አለበት ማለትም ኦርጅናል ሰነዶች በሙሉ ኮፒ ተደርገው በኮፒ ፖስታ መገኘት አለበት። ይህንን መመሪያ ተግባራዊ የማያደርጉ ተጫራቾች ከውድድሩ ወጪ ይሆናሉ።
9. ይህ ጨረታ ሰነድ ሽያጭ የሚያበቃዉ በ10ኛዉ ቀን 10፡00 ሲሆን የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋውም በ10ኛዉ ቀን 11፡00 ይሆናል። ጨረታው በግልጽ የሚከፈተው በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወይም ባይገኙም በግልፅ ይከፈታል።
10. የጥገና ስራዎችን በተመለከተ እስፔስፍኬሽን በክፍለ ከተማ ባለሙያዎች የወጣ ሲሆን ተወዳዳሪዎች በጠቅላላ ድምር አነስተኛ ዋጋ አሸናፊ ይሆናል። በጨረታ መሙያው ሰነድ ላይ ዋጋ አለመሙላት ወይም በዶ መተው ተጫራቹን ከውድድር ውጭ ያደርጋል።
11. የአልትራ ሳውንድ ባለሙያ ተወዳዳሪዎች ዝርዘር መወዳደሪያዎች መስሪያ ቤቱ ከሚሸጠው የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ መሆኑን እንገልፃለን።
12. የካፍቴሪያ አገልግሎት ጨረታ ተወዳዳሪዎች ዝርዘር መወዳደሪያዎች መስሪያ ቤቱ ከሚሸጠው የጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገኝ መሆኑን እንገልፃለን።
13. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን አላቂ ዕቃዎች ለመለየት የሚያስችል ናሙና ጨረታው እስከሚዘጋበት ሰዓት ድረስ ናሙናውን በመስሪያ ቤቱ 4ኛ ፎቅ በሚገኘው የግዥ ቢሮ 407 ገቢ ማድረግ አለባቸው። ናሙና ያላቀረበ ተወዳዳሪ ተጫራች ከውድድሩ ወጪ ይሆናል። ቋሚ እቃዎችን በተመለከተ ለማቅረብ ቀላል የሆኑትን በማቅረብ ወይም ደረጃቸውን የሚገልጽ እስፔስፊክሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸዉ።
14. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
15. መ/ቤቱ ጨረታን ከውል በፊት 20% ጨምሮ ወይም 20% ቀን መግዛት ይችላል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 154 6900 / 011 54 6029/ 011 126 8048 / 47 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክ/ ከተማ አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ ጃምቦ ህንጻ ፊት ለፊት
የጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-08-31
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛዉ ቀን 11፡00
- Bid opening: 2026-09-01 09:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው (በአስራ አንደኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Gulile Sub City Woreda 8 Adisu Gebya Health Post
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 250.00 ብር በሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 20, 2026)
- Posted at: 2026-08-20T10:10:31.000Z