Insurance Service

የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀላል፣ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኢንሹራስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎት

ግዥ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ቁጥር አኮኃ/የተ/የግ/ማ/ግጨ/አግ/5/2018

የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር የቀላል፣ ከባድ ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ኢንሹራስ ዋስትና አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፣

3. የግዥው መጠን ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

5. የኢንሹራንስ ዋስትና አገልግሎቶችን ዓይነትና የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም በኩባንው ዌብሳይት ማግኘት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች ለሚወዳሩበት ኢንሹራንስ ዋስትና ሽፋን አገልግሎት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የገንዘብ መጠን ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር ብቻ) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ስም በማሰራት ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

7. ተጫራቾች የመጫረቻ ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ አሸገው ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግዥና አቅርቦት ክፍል ቢሮ ቁጥር 19 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበትበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ኛው ቀን ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው 15 ተከታታይ ቀን አየር ላይ ይውላል፡፡

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር በሚገኘው ግዥና አቅርቦት ክፍል ቢሮ ቁጥር 19 15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ታሽጐ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡

9. በጨረታው የሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች በአማራ ክልል በዞን ከተሞች ቢያንስ 1/አንድ/ የኢንሹራንስ ዋስትና ሰጪ ቅርንጫፎች ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

10. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

11. በጨረታው መሳተፍ ለሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ዓባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር ግዥና አቅርቦት ክፍል ቢሮ ቁጥር 19 ድረስ በአካል በመገኘት፣

በስልክ ቁጥር 0912 993 321 / 0918 762 298 በመደወል ወይም

email: [email protected] ,

Telegram: http://t.me/abayconstructionplc ,

Web: www.abayconstruction.com ማግኘት ይቻላል፡፡

የአባይ ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር


Tender details

  • Deadline: 2026-09-04
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-04 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Abay Construction P.L.C.
  • Bid bond: 300,000.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 21, 2026)
  • Posted at: 2026-08-21T11:23:44.000Z
← Back to all tenders