Equipment and Accessories
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ መስያ ቁጥር 001/2019
በአዲስ አበባ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት ሎት1 የቋሚ ንብረት፣ ሎት 2. አላቂ ንብረት፤ሎት 3.የፅዳት እቃዎች፤ ሎት 4 የሰራተኛ ደንብ ልብስ፣ ሎት 5.የህትመት ስራዎች ሎት 6 መዲሀኒት፤ 7.የጥገና መሳሪያዎች እና ሥራዎች ሎት 8.የሰራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት፤ ሎት 09. በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት /NETWORK INFRASTRUCTUTRE/ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩበትን ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡-
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው፣
4 ተጨማሪ እሴትታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ C.PO. ማቅረብ አለባቸው።
|
የሎት ቁጥር |
የእቃ ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
|
ሎት 1 |
የቋሚ ንብረት |
ብር 12,000.00 |
|
ሎት2 |
አላቂ ንብረት |
ብር 6,000.00 |
|
ሎት3 |
የፅዳት እቃዎች |
ብር 4,000.00 |
|
ሎት4 |
የሰራተኛ ደንብ ልብስ |
ብር 5,000.00 |
|
ሎት5 |
የህትመት ስራዎች |
ብር 5,000.00 |
|
ሎት6 |
መዲሀኒት |
ብር 15,000.00 |
|
ሎት7 |
የጥገና መሳሪያዎች እና የጥገና ስራዎች |
ብር 4,000.00 |
|
ሎት8 |
የሰራተኛ ደንብ ልብስ ስፌት |
ብር 4,000.00 |
|
ሎት9 |
በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት NETWORK INFRASTRUCTUTRE/ |
ብር 15,000.00 |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 300.00./ሦስት መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 405 እየቀረቡ መግዛት ይቻላሉ።
7. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 303 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ጨረታው በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ታሽገዉ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይካሄዳል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
10. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ናሙና የማይቀርብባቸው እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት ድርጅቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
12. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብት የተጠበቀ ነው።
13. ለጥቃቂንና አነስተኛ ተጫራቾች የድጋፍ (የዋስትና) ደብዳቤ ከተሰጠበት አካል ደብዳቤዉ በፅሕፈት ቤቱ ኃላፊ የፀደቀ እና የፅፈት ቤቱ ኃላፊ ቲተር ያለው መሆን አለበት ፤ ከዛ ዉጭ የማንቀበል መሆኑን እናሳዉቃለን።
14. የመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡-ከአያት አደባባይ አራብሳ ኮንዶሚኒየም በሚጭኑ ታከሲዎች ተሳፍረዉ ትምህርት ቤት ማዞሪያ የሚለዉ ቦታ ላይ በመዉረድ 300 ሜትር ገባብለው ማግኘት ይችላሉ።
ስልክ ቁጥር +251-11 612 4407 በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-01
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Lemi Kura Sub City Administration Woreda 04 Arabsa Health Post
- Buyer address: በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ወረዳ 04 አራብሳ ጤና ጣቢያ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: በየሎቱ 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T09:00:38.000Z