Spare Parts and Car Decoration Materials

የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥና የጽ/መሳሪያ፣ የእንስሳት መድሃኒትና ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር C02/2019

በአብክመ የኦሮ/አስ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ስር ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውል

  • የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች ለአንድ ዓመት የሚቆይ ግዥና
  • የጽ/መሳሪያ
  • የእንስሳት መድሃኒትና
  • ፈርኒቸር ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊዎች ለመግዛት ይፈልጋል።

 በዚሁ መሠረት የእቃዎች ዝርዝር በየሎቱ ከዚህ በታች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል -

  • ሎት 1 የተለያዩ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች ለአንድ ዓመት
  • ሎት 2/ በኪሎ ሜትር የሚቀየሩ የተለያዩ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎች
  • ሎት 3/ የጽ/መሳሪያ ግዥ
  • ሎት 4 የእንስሳት መድሃኒት ግዥ
  • ሉት 5 የፈርኒቸር ግዥ
  • ሎት 6/ የእንስሳት ህክምና እቃ

ሲሆኑ መስፈርቶቹን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ስንገልጽ።

  1. ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ የታደሰና ሀጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ተመዝጋቢ ምስክር ወረቀት የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለሚያቀርቡት /ለሞሉት/ አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ ማለትም በሎት1 ለተጠቀስው እቃዎች 100,000 ብር በሎት 2 ለተጠቀሰው እቃዎች 20,000 ብር በሎት 3 ለተጠቀሰው እቃዎች 50,000 ብር በሎት 4 ለተጠቀሰው እቃዎች 15,000 ብር በሎት 5 ለተጠቀሰው እቃ 15,000 ብር በሎት 6 ለተጠቀሰው እቃ ብር 15,000 በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/C.PO/ ወይም በገቢ ደረሰኝ ወይም በመ/ቤታችን የመደበኛ በጀት ማስፈፀሚያ ኢት.ንግድ ባንክ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000160693766 በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ስም በምርጫቸው በአንዱ ከዋናው ኦርጅናል የመወዳደሪያ ሠነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  3. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከ-17/12/2018 ዓ/ም ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 10ኛው ቀን ማለትም 27/12/2018 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በመቅረብ በእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300/ ሦስት መቶ ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን ዋናና ቅጂ ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ ጨረታው ታትሞ ከወጣበት ቀን ከ17/12 /2018 ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን ማለትም እስከ 28/12/2018 ዓ/ም 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ስዓት ተዘግቶ 4፡30 በግልጽ ይከፈታል። የመክፈቻው እለት የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።
  6. ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት ጨረታውን በነጠላ ዋጋ ወይም በጥቅል/በሎት/ የሚያወዳድር መሆኑን እናሳውቃለን።
  7. የጨረታው ውጤት ለአሽናፊ ድርጅቶች በአድራሻ ለተሸናፊዎች ደግሞ በግልባጭ በደብዳቤና በመ/ቤቱ የውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
  8. ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  9. መስሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ለበለጠ መረጃ ከተጫራቾች መመሪያ ላይ መረዳት ይቻላል ወይም በስልክ ቁጥር 09 10 37 87 37 እና 09 12 03 93 15 በመደወል መጠየቅና መረዳት ይቻላል።

አድራሻችን ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ መንገድ 300 ኪ/ሜ ላይ እንገኛለን።

አብክመ በኦሮሞ አስ/ዞን የአርጡማ ፉርሲ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Artuma Fursi Woreda FEDB
  • Buyer address: ወሎ መስመር ከአዲስ አበባ 300 ኪሜ ርቀት ጨፋ ሮቢት ከተማ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:09:12.000Z
← Back to all tenders
Could not load content