Equipment and Accessories

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት አመት የሚያሥፈልጉ ዕቃዎች በግዥ መለያ ቁጥር1/2019 ማለትም

  • በሎትı ቋሚ ዕቃዎች
  • ሎት2 የጥገና (የህንፃ መሳርያ) ዕቃዎች፣
  • ሎት3 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
  • ሎት4 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች፣
  • ሎት5 የደንብ ልብስ እና አልባሳት
  • ሎት6 መድሃኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች፣
  • ሎት 7ሎት.ህትመቶች፣
  • ሎት8. የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች እና የህክምና ዕቃዎች ሰርቪስ፣
  • ሎት9.የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • ሎት 10 ለተለያዩ ዝግጅቶች ሙሉ የምግብ አቅርቦት እና
  • ሌሎችም በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ የጨረታ ማስከበሪያ ብር

ሎት ቁጥር

የጨረታው አይነት

ጨረታ ማስከበሪያ የብር መጠን

 

ሎት 1

ቋሚ ዕቃዎች

17,970.00

በተቋሙ ስፔስፍኬሽንና በፎቶ

ሎት 2

የጥገና (የህንፃ መሳርያ) ዕቃዎች

10,200.00

ናሙና የሚቀርብ

ሎት3

አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

15,000.00

ናሙና የሚቀርብ

ሎት4

አላቂ የፅዳት ዕቃዎች

14,400.00

ናሙና የሚቀርብ

ሎት5

የደንብ ልብስና አልባሳት

14,555.00

ናሙና የሚቀርብ

ሎት6

መድሃኒቶችና የላብራቶሪ ሪኤጀንቶች

81,799,895.00

 

ሎት7

ህትመቶች

10,000.00

በመ/ቤቱ ናሙና

ሎት8

የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የህክምና ዕቃዎች ሰርቪስ

1,200.00

የስራውን ሰነድ በመግዛት

ሎት 9

የመኪና መለዋወጫ ዕቃዎች

14,000.00

ናሙና የሚቀርብ

ሎት 10

ለተለያዩ ዝግጅቶች ሙሉ የምግብ አቅርቦት

10,0000

 

በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህም መሰረት።

  1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ የአቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ አምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ወረዳ 09 ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 11 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጤና ጣቢያው መሰብሰብያ አዳራሽ ጨረታው ይከፈታል። ነገር ግን የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በዓል ቀን ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን በተባለው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  4.  ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በጤና ጣቢያው ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 11 ለጨረታ በተዘጋጀ ውሳጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት የመ/ቤቱ ፍላጎት (ስፔስፍኬሽን) ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች በጥንቃቄ በስፔስፍኬሽኑ መሰረት ብቻ መሞላት አለበት፡፡ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ሎቶች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
  7. የዘገየ ጨረታና በጨረታው መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  8. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስርያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  9. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 9 ጤና ጣቢያ ሳሪስ ካዲስኮ ዝቅ ብሎ ቴሌ ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 011 470 8252/ 011 440 6261

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ የወረዳ 09 ጤና ጣቢያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-02
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-02 10:30
  • Bid opening (note): የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 11ኛው ቀን እስከ ጥዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Nifas Silk Lafto Sub City Woreda 09 Health Post
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 150.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
  • Posted at: 2026-08-24T09:22:26.000Z
← Back to all tenders