Pharmaceutical Products
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ፦
1. በመስኩ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው።
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ማስረጃ ያላቸው።
3. የዕቃ አቅራቢነት ምዝገባ ሠርትፍኬት
4. ሌሎችም ማስረጃዎች ካሉ በማያያዝ ማቅረብ የሚችልና ዕቃውን ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ድረስ የሚያቀርብ ድርጅቱ ከሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናውን 7000 /ሰባት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚጠበቅባቸውና የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋ ጽ/ቤቱ ባዘጋጀው ፎርማት ላይ ብቻ በመሙላት ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር ከላይ የተገለጸውን ማስረጃዎች ጭምር በፖስታ በማሸግ ቢሮ ቁ. 14 በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል። የሚቀርበው ዋጋ የመንግሥት ክፍያን ያካተተ መሆን አለበት።
ጨረታውም 10ኛው ቀን የሥራ ቀን ባይሆን በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተሞላው ዋጋ በአሃዝ ማይነበብ ከሆነ በፊደል የተጻፈው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በዕለቱ አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉለውም።
ማሳሰቢያ፡- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ሀድያ ዞን ሌሞ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-02
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-02 14:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Central Ethiopia
- Publishing entity: Hadiya Zone Lemo Woreda Finance and Economic Development Bureau
- Bid bond: 7,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 23, 2026)
- Posted at: 2026-08-24T09:36:14.000Z