Catering and Cafeteria Services
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓ.ም የምግብ አገልግሎት የሚሰጡ ህጋዊ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተወዳዳሪዎች ሟሟላት ያለባቸው መስፈርቶች/የተጫረቾች መመሪያ/፡፡
1.1 ማንኛውም ድርጅት/ግለሰብ እና በዘርፉ የተሰማሩ ጥቃቅን እና አነሰተኛ ኢንተርፕራይዞች ህጋዊ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑን ግብር የገበረ እና ማሰረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
1.2. ተጫራቾች ቫት ተመዝጋቢ እና የተጨማሪ እሴት ታከለ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት፡፡
1.3. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል አዳማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1054511561211 በማስገባት ጨረታው ከወጣበት የስራ ቀን ጀምሮ አዳማ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
1.4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለምግብ አቅርቦት 50000.00 /ሃምሳ ሺህ/ ብር በባንክ ቼክ የተረጋገጠ ሲፕኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
1.5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ጨረታው አይሰተጓጎልም ሆኖም 6ኛው ስራ ቀን በዓል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
1.6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴከኒካል እና ፋይናንሻልን በታሽገ ኢንቨሎፕ ኮፒውን እና ኦርጅናሉን በተናጠል በማቅረብ አዳማ ከተማ ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ቢሮ 5ኛ ፎቅ በመቅረብ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን ማስገባት ይችላሉ፡፡
1.7. አትሌቲክስ ክለብ በአሰላ ካምፕ ለ100 አትሌቶች መመገብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
1.8. ለአትሌቲክስ ምግብ በሚዘጋጅበት አደራሽ ውስጥ ከአልኮል መጠጥ፣ ከተለያዩ ሱስ አስደዛዥ ዕፆች ፣ጭፈራ ቤት እንዲሁም ስፖርተኛን ሊረብሹ የሚችሉ የራቀ መሆን አለበት፡፡
1.9.ተጫራቾች በቂ የማድ ቤት እና የምግብ ቁሳቁስ ከበቂ የሰው ሃይል ጋር ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡
1.10.ተጫራቾች በ20 ዓም በዚህ የስራ ዘርፍ ተሰማርተው እየሰሩ ያሉ መሆኑን የሚገልፅ የስራ ልምድ ከንግድ እና ገበያ አግልግሎት ፅ/ቤት እና ሲሰሩ ከነበረበት ቦታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1.11. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ :- 0223311250/0911941978
የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ
Tender details
- Deadline: 2026-09-04
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-04 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: የአዳማ ከተማ አትሌቲክስ ክለብ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 24, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T08:12:48.000Z