Equipment and Accessories

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሞተር ሳይክል፣ እስቴሽነር እና ፈርኒቸር ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር ግልጽ 01/2018

የዕቃ አይነት

  • ሎት 1 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 2 ሞተር ሳይክል
  • ሎት 3 እስቴሽነር
  • ሎት 4 ፈርኒቸር

በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመስኩ ከተሰማሩ ነጋዴዎች ሎት1፣ሎት2፣ ሎት3 እና ሎት 4 የተዘረዘሩትን ዕቃዎችን ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች ሁሉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በሟሟላት መሣተፍ ይችላሉ።

  1. ከላይ በተጠቀሱት ለመወዳደር በየዘርፍ ሥራዎች የተሰማሩ፡ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2.  በገቢዎች ሚኒሰቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ፤
  3.  ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና ሎት2 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ እና ለሎት3 እና ሎት4 ብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ባንክ ጋራንቲ ወይም ሰፒኦ /CPO/ ማስያዝ አለበት።
  4. አሸናፊ ተጫራች ውሉን ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
  5. ተጫራች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 አስር/ የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሴሚናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖም ልማት መምሪያ በቢሮ ቁጥር 02 ግ/ፋ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቀርቦ የጨረታ ሠነዱን የንግድ ፈቃዳቸውን በማሳየት 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ በመከፈል መግዛት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዳቸውን ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያዩ ኤንቨሎፕ ውስጥ በሰም በማሸግ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች ቴክኒካሉና ፋይናንሻሉን በተለያዩ ኤንቨሎፕ ከታሸገ በኋላ በአንድ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ማሸግ አለባቸው። በዕለቱ ሎት እና ሎት2 ቴከኒካሉ ክፍል ብቻ ይከፈታል።
  8. የጨረታ ሳጥንም ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት በ11 (አስራ አንደኛ) የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይታሸጋል።
  9.  ይህ ጨረታ ከተሞላበት ቀን ጀምሮ ዋጋ የሚፀናበትን ከ45 ቀናት በታች የጊዜ ገደብ መስጠት የለበትም።
  10. ጨረታው በአሰራ አንደኛው ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ ከ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ግዥ/ፋ/ን/አስ ዳይሬክቶሬት ይከፈታል።
  11. ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ቢሮ ጨረታውን የሚከፍት መሆኑን ይገልጻል።
  12. አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ባሉት በ7 ቀናት በኃላ ቀርቦ ውሉን መፈረም ይኖርበታል።
  13. አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን እያንዳንዳቸዉን እቃ ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ቀናት በራሱ የማጓጓዣ ወጪ ቢሮ ድረስ በማቅረብ በተፈለገዉ በተጠየቀዉ ስፔስፍኬሸን መሆኑን በባለሙያ ከተጣራ በኋላ ማስረከብ አለበት።
  14. አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንዳጠናቀቀ ከፍያው ወዲያውኑ በቼክ እና ባንክ ዝውውር ይከፈለዋል።
  15.  አቅራቢው የውል ግዴታውን ሙሉ በሙሉ አለመፈፀሙ ሲረጋገጥ በውል ግዴታው መሰረት በህግ አግባብ ይቀጣል።
  16. ቢሮ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

ለተጨማሪ መረጃ የግዥ፣ፋይናንስና ንብረት ዳይሬክቶሬት

የስልክ ቁጥር 0916037038

አድራሻ፦ ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ህንጻ ውስጥ (ሀዋሳ)

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-05 14:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛው ስራ ቀን ከ8፡30 ሰዓት
  • Region: Sidama
  • Publishing entity: የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
  • Posted at: 2026-08-26T10:22:36.000Z
← Back to all tenders