Equipment and Accessories
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት በ2019ዓ.ም የስራ ዘመን የተለያዩ እቃዎችን በ1ኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ሎት1 ቋሚ አቃ ኤሌክትሮኒክስ (6313) ሎት2. የደንብ ልብሶች (6211) ሎት3 የጽህፈት መሳሪያና ሌሎች (6212) ሎት 4 አላቂ የትምህርት እቃዎች (6215) ሎት5.የተለያዩ መሣሪያዎች እና መፃህፍት (6219) ሎት6 ሌሎች አላቂ እቃዎች (የፅዳት እቃዎች (6218) ሎት7 ቋሚ እቃዎች (6314) ሎት8 የህከምና እና የላብራቶሪ እቃዎች (የቤተ-ሙከራ) (6214) ሎት9 የህትመት ስራዎች(6213) ሎት 10. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና(6243)
1. የጨረታው ቁጥር 01/2019ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።
2. ተጫራቾች ለአቅርቦቱ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ነምበር ሊኖራቸው ይገባል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ በእያንዳንዱ ሎት 200ብር በመከፈል ዘወትር በኮ/ቀ/ክ/ ከ/ወ/11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለውቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10(አስር) የስራ ቀናት እሁድና ቅዳሜን ሳይጨምር ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ምሳ ሰአትን ሳይጨምር ማግኘት ይችላሉ።
5. አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ሌላው ተንተርሶ መስጠት አይችልም።
6. ገዢው ለሚገዛው ግዢ 20% ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
7. ተወዳደሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል ) ሰነዶች ለየብቻ በታሸገ ፖስታ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ (ቢሮ) ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰአት ከ02፡30-11፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ተዘግቶ በዛው ቀን ከጠዋቱ 04፡30 ይከፈታል።
9. የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ሀላፊ ከምና ፊርማ እንዲሁም አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት።
10. አሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ በተመለከተው ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% በሲፒኦ አስይዘው ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
11. መስሪያ ቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. በጨረታ ሰነድላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሁፍ ከጨረታው መክፈቻ 2ወይም 3 ቀናት በፊት ማቅረብ ይችላሉ።
13. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ላይ ቅሬታ ካላቸው በት ቤቱ ግዢ ክፍል የስራ ሂደት ቅሬታውን በፅሁፍ ማቅረብ ይችላሉ በዚህ ክፍል የማይፈታ ከመሆነ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ። የጨረታው ውጤት በተገለፀ 7ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ከአሸናፈው አካል ጋር ውል ይፈፅማል።
14. አሸናፊው ድርጅት የግዢውን ውል ከፈረሙበት ቀን ጀምሮ ባሉ 10 የስራ ቀናት እቃውን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባትም ሆነ ለማጭበርበር የሚሞከር ማንኛውም ተጫራች ከጨረታው ውጭ ይሆናል።
16. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት።
17. የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 (13,200) ለሎት 2(7,300) ለሎት 3 (7,400) ለሎት 4(6000) ለሎት 5(10,000) ለሎት 6(7,000) ለሎት 7(14,200) ለሎት 8(7,500) ለሎት 9(1600) በሎት 10 (750) የጨረታ ማስከበሪያ የግድ በሲፒኦ መሰራት አለበት ጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም።
18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
19. በመንግስት የተደራጁ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ካደራጃቸው ፅ/ቤት በሀላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ብቻ ይዘው ሲመጡ ይስተናገዳሉ።
20. ነጋዴዎች ሳምፕል ለሚገቡ እቃዎች ሳምፕል እንዲያቀርቡ እና ለቋሚ እቃዎች በፎቶ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርበታል።
አድራሻ፡-በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳስፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻው እንዳለፉ ባለው ቅያስ ጠደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው በት/ቤቱ ቅጥር ጊቢ ውስጥ በሚገኘው በቢሮ ቁጥር 03 ፋይናስ ክፍል
በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-08
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00
- Bid opening: 2026-09-08 12:00
- Bid opening (note): ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ajamba Primary School
- Buyer address: በኮ/ቀ/ክ/ከ/ወ/03 አጃምባ የመ/ደ/ት/ቤት ካራ ቆሬ ታክሲ ተራውን እንዳለፉ ወደ አጃምባ መውጫ ባለው መንገድ ብሎኬት ማምረቻውን እንዳለፉ ባለው ቅያስ ወደ ቀኝ 200 ሜትር ገባ ብሎ
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published on: Addis Zemen (Aug 25, 2026)
- Posted at: 2026-08-26T10:58:39.000Z