Equipment and Accessories
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የተሽከርካሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Amhara
Description
ግልጽ ብሔራዊ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ከዚህ በታች የተገለጹትን የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች እና የተሸከርካሪ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ሎት |
የኮምፒዩተሮች ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
ጨረታ ቁጥር |
|
1 |
ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር |
300,000.00 |
ኢኤአ -ባሪ/ግብጨ/002/2019 |
|
2 |
A-4 ወረቀት እና ሌሎች የጽሕፈት መሳሪያዎች |
200,000.00 |
ኢኤአ -ባሪ/ግብጨ/003/2019 |
|
3 |
የፕሪንተር ቀለም |
150,000.00 |
ኢኤአ -ባሪ/ግብጨ/004/2019 |
|
4 |
የተሽከርካሪ ጎማዎች |
175,000.00 |
ኢኤአ- ባሪ/ግብጨ/005/2019 ሎት 1 |
|
5 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች |
175,000.00 |
ኢኤአ- ባሪ/ግብጨ/005/2019 ሎት 2 |
በዚህ ጨረታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡና በመስኩ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሠነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን ዋና መ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 05 ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት ወይም ድብ አንበሳ ሆቴል ጎን በሚገኘው ህንጻ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 408 ድረስ በመቅረብ ለአንዱ ሎት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በተ.ቁ 2 በተገለጸው አድራሻ ድረስ በመቅረብ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው መስከረም 04 ቀን 2019 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0583206775/6999 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የባሕር ዳር ሪጅን
Tender details
- Deadline: 2026-09-14
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-09-14 14:30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T08:21:46.000Z