Products and Services
ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአርዘሊባኖስ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ለአርዘሊባኖስ (Arzelibanos (Casuarina equisetifolia)) ዘር ግዢ የወጣ ጨረታ
ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የአርዘሊባኖስ ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ይህንን ዘር ችግኞችን ለማፍላት ጥቅም ላይ የሚዉል ሲሆን፣ ችግኞችን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል (በማሰራጨት)፣ አርሶ አደሮቹ ዛፎችን በማልማት ሀብታቸውን እንዲጨምሩ፣ ገቢያቸውን እንዲያሰፉ እና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ (እንዲያሻሽሉ) ይደረጋል።
- አጠቃላይ የሚያስፈልገው የዘር መጠን 207,976,844 ዘሮች ሲሆን፣ ይህም በአንድ ኪ.ግ 970,000 ዘሮች እንዳሉ በመገመት ባጠቃላይ 215 ኪ.ግ የአርዘሊባኖስ ዘር ይፈለጋል።
- ይህ መጠን ዉሉ እስኪፈረም ድረስ ሊቀየር ይችላል።
- የግዢ ሂደትና ጠባይ (ዘሩ ከመሰብሰቡ በፊት ወይም ከተሰበሰበ በኋላ ከ አቅራቢው ጋር ውሉን እንፈራረማለን)
- የግዢ ሂደቱ እንደ ዘር መሰብሰቢያ የጊዜ ሰሌዳው ይለያያል። ዋን ኤከር ፈንድ በጨረታው ቀን አስቀድሞ የተሰበሰበ ዘር ሊገዛ ይችላል፣ ወይም ገና ያልተሰበሰበ ዘር ሊገዛ ይችላል።
- ዘሩ በጨረታው ጊዜ አስቀድሞ ከተሰበሰበ፣ ዋን ኤከር ፈንድ ከተመረጡ አቅራቢዎች ናሙናዎችን ይሰበስባል።
- እነዚህ ናሙናዎች በጥራት ላይ ተመስርተው ይነፃፀራሉ።
- የተመረጠው ሻጭ ዘሮችን በሚመለከተው የኳራንቲን ባለስልጣን እንዲመረመር ያደርጋል።
- ዘሩ ገና ካልተሰበሰበ፣ ዋን ኤከር ፈንድ እናት ዛፎችን እንዲመለከት ባለሙያ ይልካል።
- ባለሙያው መመሪያ ይሰጣል እንዲሁም ይመለከታል።
- ናሙናዎች ከሚሰበሰበው ዘር ይወሰዳሉ እና በሚመለከተው የኳራንቲን ባለስልጣን ይፈተሻሉ፡፡
- በጨረታው ላይ አስቀድሞ የተሰበሰበ የአርዘሊባኖስ ዘር ከሆነ ቀኑን ይጥቀሱ ወይንም ኮንትራቱ ከተፈረመ በኋላ ዘሩን ለመሰብሰብ እንደሚፈልጉ በጨረታው ላይ ይግለጹ
- የጥራት ዝርዝር መገለጫዎች፡
- ዘሮቹ ከቆሻሻ እና ከሌሎች ባዕድ ነገሮች ንጹህ መሆን አለበት
- ዘሮቹ ከሚታወቅ የአርዘሊባኖስ የዘር ምንጭ መሰብሰብ አለባቸው።
- ዘሩ ቀድሞ የተሰበሰበ ከሆነ፣ የተሰበሰበበት ጊዜ ከ 1 አመት በታች መሆን አለበት።
- ዘሩ ከመሰብሰቡ በፊት ወይም በኋላ ከአሽናፊው አቅራቢ ጋር ውሉን እንፈርማለን።
- ይህ ውል ዘሩ ሊያሟላቸው የሚገባ ልዩ የጥራት መለኪያዎችን ያካትታል።
- ዘሩ ከተሰበሰበ በኋላ እነዚያን የጥራት መለኪያዎች ካላሟላ፣ OAF( ዋን ኤከር ፈንድ) የክፍያ መጠኑን ይቀንሳል ወይም ደግሞ ውሉን ሙሉ በሙሉ ሰርዞ ማንኛውንም ቅድመ ክፍያ እንዲመለስ ያደርጋል።
እባኮትን የሚከተለውን ቅጽ ሞልተው ፈርመዉ ማህተም በማድረግ ከታች በተቀመጡት በ አንዱ ይላኩ።
- ኢሜይል [email protected]
- የቴሌግራም @oafbidsubmissions
- ለበለጠ መረጃ 0985654565 ይደውሉ።
ሁሉም ተጫራቾች እስከ መስከረም 8 2019 ዓ.ም ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ዘግይተው የሚቀርቡ ጨረታዎች ውድቅ ይሆናሉ፡፡
|
ጥያቄ |
መልስ |
|
የአንድ ኪሎ ግራም የተጣራ የአርዘሊባኖስ ዘር ዋጋ? |
|
|
ዘሩ የተሰበሰበው ቀን ወይም የሚሰበሰብበት ቀን መቼ ነው? ወሩን ጨምረው ያስገያስገቡ |
|
|
ዋን ኤከር ፈንድ የጥራት ፍተሻ እንዲያካሂድ ዘሩ ተሰብስቦ እና ተጣርቶ እንዳለቀ ወድያዉኑ ታደርሳለህ? |
|
|
የዘር ምንጭ የት ነው? ወይስ የዘሮቹ እናት ዛፎች የሚገኙት የት ነው? (ክልል እና ወረዳ) |
|
|
የዘሩ ጥራት በኮንትራቱ ላይ የተገለጹትን የ ጥራት ደረጃዎች ካላሟላ ሁኔታውን ለማሻሻል እና የጥራት ደረጃዎችን ለማሟላት ሁሉንም አስፈላጊ እርምጃዎችን ይወስዳሉ? |
|
|
215 ኪሎ ግራም (207,976,844 ዘር) ሙሉ ምርት በስንት ቀን ዉስጥ ማቅረብ ይችላሉ? በአጭር ቀን ዉስጥ ማቅረብ የሚችል የተሻለ እድል ይኖረዋል። |
|
- ዋን ኤከር ፈንድ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውንም ሻጭ አለመቀበል ወይም ማጽደቅ መብት አለው።
- ዋን ኤከር ፈንድ የኮንትራት ፊርማ ከመደረጉ በፊት ይህንን ጨረታ በማንኛውም ጊዜ ሊሰርዘው ይችላል።
- ዋን ኤከር ፈንድ ከማንኛውም አቅራቢ የተገኘውን ምርጥ ዋጋ ከሁሉም ተጫራቾች ጋር የመጋራት መብት አለው።
- ዋን ኤከር ፈንድ ለተለያዩ ሻጮች የተለያዩ መጠኖችን ሊሰጥ ይችላል።
- ዋን ኤከር ፈንድ የተጠቀሰውን መጠን ከመግዛት ሊቆጠብ ይችላል። የተጠቀሰው መጠን ውሉ ከመፈረሙ በፊት ሊለወጥ ይችላል።
- ዋን ኤከር ፈንድ ጨረታውን ወይም የጨረታውን ማንኛውንም ገጽታ ለማሻሻል እና ለማንኛውም ውሳኔ እና እርምጃ ምክንያት ሳያቀርብ በማንኛውም አቅራቢ የቀረበውን ማንኛውንም ጨረታ ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስም---------------------- ፊርማ-----------------------------
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-09-18 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: One Acre Fund
- Buyer TIN: 0041750397
- Buyer address: Yeka Sub City, Woreda 8, Level 5, Building Opposite Misrak Polytechnic College, Addis Ababa, Ethiopia Or Kebele 13, Bahir Dar, Amhara Region(Bahir Dar office)
- Published on: 2merkato.com (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T08:24:32.000Z
- Buyer website: https://oneacrefund.org/