Equipment and Accessories
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ኤሌክትሮኒክስ እና የመኪና መለዋወጫ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Sidama
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት1፡- ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት2 ፡- የመኪና መለዋወጫ ዕቃ
ስለዚህ ተጫራቾች፡
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል፣
- በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግስት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣
- የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሁሉም ዶክመንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000 (አስር ሺህ) ብር CPO (ሲ.ፒ.ኦ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሰራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል፣
- አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ C.P.O (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል፣
- ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ፤ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሸፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮው ቁጥር 507 ቀርበው በመከፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ፡-
- መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም።
- የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገናዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም። ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ መያያዝ አለበት።
- ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል።
- ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፦ 046 212 5731 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ።
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-09-12
- Bid closing time: 15:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-12 15:30
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት
- Region: Sidama
- Publishing entity: Sidama National Regional State Peace and Security Bureau
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 100.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
- Posted at: 2026-08-28T09:00:36.000Z