Vehicles Purchase

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ባለ 15 መቀመጫ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ቻርጀር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 01/18

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ባለ 15 መቀመጫ አዲስ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እና የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ ቻርጀር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በዘርፋ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ተፈላጊ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፣
  2. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀን ሲሆን ሰነድ የሚሸጠው በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 10፡30 የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው በአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 208 በመምጣት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
  3. የጨረታው ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ኦርጅናልና ኮፒ በማለት አሽጎ ማቅረብ አለባቸው፣
  4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለፀውን 200,000.00 ብር በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋሰትና ከቴክኒካል /ህጋዊ ሰነዶች/ ኦርጅናል ጋር ወይም ለብቻው በፖስታ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፣
  5. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 9፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከ9፡30 ጀምሮ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
  6. የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  7. ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ስልክ ቁጥር 0116-454147/0116-453598 /0118-694931 ከመገናኛ አያት 49 ወይም ጣፎ መንገድ ከሰዓሊተ ምህረት ማርያም ቤ/ክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ

የኢትዮጵያ ብቃትና ስራ አመራር ኢንስቲትዩት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 15:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 15:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውልና በ21ኛው ቀን 9፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Management Institute
  • Buyer address: ከሳህሊተ ምህረት ማርያም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
  • Bid bond: 200,000.00 ብር
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Aug 28, 2026)
  • Posted at: 2026-08-28T09:05:14.000Z
← Back to all tenders