Industrial Machinery Provision and Installation
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የተለያዩ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፦ ጣበስፋ/አገ/ብገጨ/02/2018/19
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ
- በሎት- የኢንክላይንድ ፍላት ቤልት ጋይድ ሮለር የኮቲንግ ስራ
- በሎት-2 የተለያዩ የፋብሪካ መለዋወጫ ዕቃዎች
- በሎት-3 የተለያዩ ኤሌክትሪካል እና ኢንስትሩመንታል መለዋወጫ ዕቃዎች
- በሎት-4 የወርክ ሾኘ ዕቃዎች እና
- በሎት-5 የሁርሰስ እና የቤል ትራክተር ከሞተር ውጭ የሆኑ መለዋወጫ ዕቃዎች እና የሞተር ክፍል መለዋወጫ ዕቃዎች
- በሎት6 የዋይ ቲኦ እና የአግሮትሮን ትራክተር መለዋወጫ ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
1. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ብቁ ተጫራቾች ሕጋዊ የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ የታክስ ክሊራንስና በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ ለተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት፤ በተጨማሪም ተጫራቾች የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ወይም ሌላ አግባብነት ያለው አካል ባዘጋጀው የዕቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው::
2. ጨረታው መስከረም 05 ቀን 209 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል፡፡ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በጨረታው መክፈቻ ላይ መገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከታች በተራ ቁጥር 4 በተገለፀው አድራሻ መስከረም 05 ቀን 2019 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ዘግይቶ የሚቀርብ የመጫረቻ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂቁጥር 100005773567 በመክፈልና የባንከ አድቫይስ በማቅረብ በተራ ቁ.4 ከተመለከተው ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታው ማስረከቢያና መክፈቻ አድራሻ ቀጥሎ የተመለከተው ነው፡፡
አዲስ አበባ ቶታል 3 ቁጥር ማዞሪያ ተዘንአ ሆስፒታል አካባቢ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ህንጻ፡፡
ብሱክ A ቢሮ ቁጥር BOO8
ስልክ ቁጥር 011 5586725 አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ የጠቅላላ ዋጋውን 2% ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ባልተመሠረተ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
6. ጨረታው ፀንቶ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ነው፡፡
7. የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ነው፡፡
ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011558-67-25 ደውሎ መጠየቅ ይችላል፡፡
ጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-15
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-09-15 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Tana Beles Sugar Factory Addis Ababa Coordination Office
- Bid bond: በየሎቱ 2%
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published on: Addis Zemen (Aug 30, 2026)
- Posted at: 2026-08-31T08:53:12.000Z