Packaging and Labelling

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ የማሸጊያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያ ቁጥር APPF/NCB/01/19

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን የማሸጊያ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  • 1. የተለያዩ Carton Label
  • 1.2. የተለያዩ Adhesive Label
  • 1.3. Carton Box 16 Lit/7kgCapacity
  • 1.4. የተለያዩ Plastic Sheet

2. ተጫራቾች የስራ ዘርፍ የሚያሳይ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ለሚከፈልባቸው ዕቃዎች የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ በመንግሥት የግብር ሕግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያሳይ ሰርቲፊኬት እና በመንግሥት ግዥ ለመሳተፍ በመንግስት የኤሌክትሮኒክ ሥርዓት ፖርታል ላይ በአቅራቢነት መመዝገቡን የሚያሳይ መረጃ እንደ ቅድመ ሁኔታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች አዳሚ ቱሉ ባለው የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ከኩዌት ኢምብሲ 10 ሜትር ገባ ብሎ ጅቡቲ ኢምበሲ ፊትለፊት ከሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር አምስት መቶ ብቻ (500.00) በመክፈል የጨረታው ማስታወቂያ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ላይ የተጫራቹ ድርጅት ስምና አድራሻ በትክክል ተፅፎ የድርጅቱ ማህተም ያረፈበት መሆን ይኖርበታል።

5. ተጫራቾች ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ኮፒ እና ኦሪጅናሉን በተለያየ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት እቃ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በተጫራቹ ድርጅት ኃላፊ ተፈርሞና ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።

7. ተጫራቾች ለጨረታ ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚ ቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ ስም የባንክ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታው የቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።

8. ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰነዱን እስከ ነሀሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ የፋብሪከው ዋና መስሪያ ቤት ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ መክፈቻው ዕለት ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ቦሌ ርዋንዳ በሚገኘው ማስተባበሪያ ቢሮ ይሆናል

9. ፋብሪካው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ፡- አ.አ ማስተባበሪያ ስልክ ቁጥር 011 662 4656 አ/አ፣ አዳሚ ቱሉ 0464419164(ማዞሪያ)፤ 0464419287 (ንግድ መምሪያ) ፓሣ.ቁ 1206 (ኢ.አ)፣ 247 (አ/ቱሉ)

በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን አዳሚቱሉ የፀረ-ተባይ ማዘጋጃ ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-05
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-09-05 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Adami Tulu Pesticides Processing Factory
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T09:28:59.000Z
← Back to all tenders