Equipment and Accessories
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገላን ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት የተለያዩ ቋሚ፣ አላቂ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የኤልክትሮኒክስ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice Furniture
Oromia
More tags
Furniture and FurnishingHouse FurnitureComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesStationeryCleaning and Janitorial Equipment and ServiceTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsAmharic2merkatoGelan City Woreda Court
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በሽገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገላን ከ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
- የተለያዩ ቋሚ፣
- አላቂ፡
- የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- የደንብ ልብስ እና
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመክፈል ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከ100,000ብር ለሆነ ግዥ የተጨማሪ እሴት ታክስ NAT/ ተመዝጋብ የሆኑና ለዚሁ መስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- በገንዘብ ሚኒስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢነት የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቶች ብቻ መካፈል ይችላሉ።
- ተጫራቾች ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 150 (መቶ ሃምሳ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ለምን ለምን ዓይነት ዕቃ እንደ ሆነ በሰነዳቸሁ ላይ በትክክል ለይተው መጻፍ ይኖርባቸዋል።
- ፍ/ቤቱ ካቀረበው መስፈርት /standard ውጪ ማቅረብ አይቻልም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ነገር መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን መሰረዝ አይችልም።
- ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት እንደ አስፈላጊነታቸው (25%) በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።
- ጨረታው የሚቆየው ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ይሆናል። በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ 4፡30 ሰዓት ተጫራቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። እለቱ የስራ ቀንካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- ማንኛውም ተጨራች በጨረታ ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ባቀረበው ጠቅላላ ዋጋ ላይ 1% የጨረታ ማስከበርያ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ፍ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የጨረታው ዋጋ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ መጥቀስ ይኖርበታል።
- ፍ/ቤቱ የሚያጫርታቸውን ዕቃዎች ብዛት ለተከታታይ 6 ወራት ውል ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ይዋዋላል።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሠጠው እስፔስፊኬሽን መሠረት ተሞልተው ካልቀረቡና ማንኛውም ዓይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ድርጅት ነው።
አድራሻ፡- በገላን ከተማ ማዘጋጃ ቤት ፊትለፊት በሚገኝ የፍርድ ቤቱ ፎቅ ላይ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡ 011 887 1269 / 09 22 81 70 19
በሸገር ከተማ ከፍተኛ ፍ/ቤት የገላን ክ/ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-17 10:30
- Bid opening (note): ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 11፡30 ተዘግቶ በነጋታው በ 4፡30 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Gelan City Woreda Court
- Bid bond: 1%
- Bid document price: 150.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Aug 31, 2026)
- Posted at: 2026-09-01T10:07:26.000Z