Catering and Cafeteria Services

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል

Description

የመዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት

ግዥ ግልጽ ጨረታ

ኮ /ዲ /ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/33/2018

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት ለሠራተኞች መዝናኛ ክበብ የምግብና ተያያዥ አገልግሎት የሚሰጥ ድርጅት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ውል ይዞ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም:-

  1. በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ ብር) በመከፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2.  ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000.00 ብር /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (un- conditional bid bond guarantees) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
  4. ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 0921022581/0912339977

አድራሻ: ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፌት ከሲ.አር.ዲ.ኤ አጠገብ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-12
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-12 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
  • Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 01, 2026)
  • Posted at: 2026-09-01T13:47:43.000Z
← Back to all tenders