Equipment and Accessories

በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ኤሌክትሮኒክስ፣ ፈርኒቸር፣ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ እና የተለያዩ የሞተር የመኪና ጎማዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት በወረዳዉ ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች 1ኛ ዙር በ2019 የበጀት ዓመት ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ማለትም

  • ኤሌክትሮኒክስ
  • ፈርኒቸር
  • የጽህፈት መሳሪያዎች
  • የፅዳት ዕቃዎች
  • የደንብ ልብስ
  • የተለያዩ የሞተር የመኪና ጎማዎች

በግልጽ ጨረታ ህጋዊና አቅም ያላቸዉን ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጸዉን መመሪያ መስፈርት/ በመከተል ይህን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

1. ተጫራቾች በጨረታዉ ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመኑን (2018/2019) ግብር የከፈሉ እንዲሁም የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸዉና ቫት ከፋይ የሆኑ ዝ Number ማቅረብ የሚችሉ።

2. ማንኛዉም ተጫራች ወደ ጨረታዉ ሂደት ከገባ በኋላ በሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛዉም ሁኔታዎች ማሻሻል መቀየር እንዲሁም ሀሳቤን ቀይሪአለዉ ማለት አይችልም።

3. ማንኛዉም ዕጩ ተወዳዳሪ የጨረታዉን ሂደት ለማስተጓጎል ቢሞክር ከጨረታዉ ዉጭ እንዲሆን ተደርጎ ወደፊት በሚደረገዉ የመንግስት ግዥ ላይ እንዳይሳተፍ የሚደረግ እና ያስያዘዉ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ የሚሆን ይሆናል።

4. ማንኛዉም ተጫራች በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ እንዲችል የሚገልጽ ከህጋዊ አካል የተሰጠ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት።

5. ተጫራቾች በሚሰሩበት የንግድ እና በንግድ ፍቃዳቻዉ ዘርፍ ብቻ ነዉ መወዳደር የሚችሉት፡፡

6. ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ የግዥ መደብ ብር 10,000 /አስር ሺህ/ በባንክ በተመሰከረለት CPO ማቅረብ አለበት ነገር ግን በካሽ ከሆነ ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኢንታዬ ቅርንጫፍ ገቢ ተደርጎ computer generated slip መቅረብ አለበት፡፡

7. ተወዳዳሪ ድርጅቶች የዕቃ ጥራት ደረጃቸዉ አስቸጋሪ የሆኑ የዕቃ አይነቶችን መስሪያ ቤታችን ቀድሞ ስላዘጋጀ ለምሣሌ የኮምፒውተር ወረቀት፣ እስክሪብቶዎች፣ ኬንት፣ ሶፍት፣ ኡሁ ፣ አጀንዳ፣ የኮምፒዉተር ቀለም ኦርጅናል፣ የቆዳ ዉጤቶች ቦርሳዎች እና ሌሎችም ተወዳዳሪ ድርጅቶች ይህን ናሙና መሰረት በማድረግ ብቻ የምንቀበል መሆኑን በጥብቅ አናሳስባለን።

8. አሸናፊዉ ድርጅት ዕቃዉን ጭነዉ እስከ መ/ቤታችን ግምጃ ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

9. ተጫራቾች ዕቃው የተሰራበትን /የተመረተበትን ሀገርና የጥራት ደረጃ የመስራት አቅሙን እንዲሁም ሞዴሉንና የተመረተበት ዓ.ም መግለፅ አለባቸው።

10. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል በተለያዩ ፖስታ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው።

11. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋዉን መሙላት ያለባቸዉ በተሸጠላቸዉ ሰነድ ላይ ብቻ መሆን አለበት እንዲሁም እያንዳንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆን አለበት :: በራሳቸዉ ሰነድ ላይ የሚሞላ ለስራችን አመቺ ስለማይሆን ተቀባይነት የለዉም።

12. ጽ/ቤታችን የሚያጫርታቸዉን ዕቃዎች አስከ 20% በመጨመር ወይም በመቀነስ ማዘዝ ይችላል።

13. ተጫራቾች በሰነዶቻቸዉ ላይ ስማቸዉን፣ ሙሉ አድራሻቸዉን፣ ስልክ ቁጥራቸውን በትክክል ጽፈዉ መፈረምና ማህተም ማድረግ አለባቸዉ።

14 .ተወዳዳሪዎች የሚሰጡት የጨረታ ዋጋዉ ጨረታዉ ከተከፈተ ቀን ጀምሮ ለ 60 ቀናት ወይም ለሁለት ወር ፀንቶ የሚቆይ መሆን አለበት።

15. መ/ቤቱ ጨረታዉን ገምግሞ ለማሳለፍ ወይም ዉድቅ ለማድረግ የሚጠቀምበት ዘዴ እንደ ዕቃዉ አይነት ወይም የሚፈለገዉ አገልግሎትን መሰረት በማድረግ ጥራትን ወይም ዋጋን ከግንዛቤ በማስገባት ተወዳዳሪዎችን አሸናፊ ወይም ዉድቅ የሚያደርግ ሲሆን ሁለት እኩል ዋጋ ቢያቀርቡ ዕጣ ተጥሎ የሚሰጥ ይሆናል።

16. የሰነዱ ሽያጭ የሚቆይበት ቀን 27/12/2018 እስከ 13/01/2019 ሲሆን፡ በ 11፡30 ላይ ሳጥኑ ተዘግቶ ጨረታዉ የሚከፈተዉ በ14/1/2019 ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቹ ወይም ህጋዊ ወኪሉ በተገኘበት በወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 01 በይፋ ይከፈታል።

17. የጨረታ ሰነዱን ዝርዝር በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ከወንዶ ወረዳ ገንዘብ ፅ/ቤት ሰነድ ሽያጭ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ) በወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በባንክ መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ስሊፕ በመያዝ ቢሮ ቁጥር 01 ሰነዱን መግዛት የሚቻል ሲሆን ተወዳዳሪ ደርጅቶች ሰነድ ከገዙበት ቀን ጀምሮ በተዘጋጀለት የጨረታ ሳጥን ዉስጥ በስራ ሰዓት የሰነዱ ሽያጭ እስከሚያበቃበት ቀን ድረስ ማስገባት ይችላል።

18. የጨረታ ዉል ከጨረታ ሰነድ ጋር ስለሚሸጥ በዉሉ መሰረት ጨረታ ያሸነፈው ነጋዴ ለዉሉ ተገዥ መሆን አለበት።

19. ማንኛዉም ተጫራች ከቫት ዉስጥ 7.5% እና (3%)ለወረዳ የሚቆርጥ ይሆናል።

20. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

21. አሸናፊ ድርጅቶች ካሸነፉት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 10% የዉል ማስከበሪያ በባንክ ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መደበኛ ሂሳብ ቁጥር 1000205079606 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ ማድረግ አለበት።

ለበለጠ መረጃ 046 1140006/0461140011 ሞባይል 09 11043416,0936459025

በምዕራብ አርሲ ዞን ወንዶ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid opening: 2026-09-24 10:30
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: West Arsi Zone Wendo Woreda FEDB
  • Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 1000.00 /አንድ ሺህ ብር/
  • Published on: Addis Zemen (Sep 02, 2026)
  • Posted at: 2026-09-02T08:09:59.000Z
← Back to all tenders