Equipment and Accessories
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsMechanical
Dire Dawa
More tags
Construction Machinery and EquipmentConstruction and Water WorksHand Tools and Workshop EquipmentIndustrial Machinery Provision and InstallationComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesMaterialsEducation and TrainingBuilding and Finishing MaterialsHotel Service ProvisionHospitality, Tour and TravelOtherConsultancyICTOrganizationalAmharic2merkatoEthio-Italian Poly Technique College in Dire Dawa Administration
Description
የ1ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ
የጨረታ መለያ ቁጥር 01/2019
በድሬዳዋ አስተዳደር የኢትዮ-ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም ከተመደበለት በጀት ላይ የሚከተሱትን፦
- ሎት - 01 የአውቶሞቲቭ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
- ሎት - 02 የኮንስትራክሽን የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
- ሎት - 03 የኤሌከትሪክ ኤሌክትሮኒክስ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
- ሎት - 04 የሆቴል ቱሪዝም ሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
- ሎት–05 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የሥልጠና ዕቃዎች ግዥ
- ሎት- 0 6 የማኑፋክቸሪንግ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
- ሎት- 07 የሰርቬይንግ የሥልጠና ዕቃዎች ግዢ
በዚሁ መሠረት በጨረታው ላይ መወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ ሕጋዊ የሆነና የታደሰ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ባዘጋጀው የዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና በተወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ላይ የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠና በጨረታ ላይ ማሳተፍ የሚያስችል የዕቃ አቅራቢነት ማስረጃ (ደብዳቤ) ማቅረብ አለባቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) የሚገልፁ የምስክር ወረቀት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ማቅረብይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የዕቃዎች ዋጋ በገዙት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ በሚታይ መልኩ ያለስርዝ ድልዝ በመሙላት የሞሉት ዋጋ በኢትዮጵያ ብር ሆኖ ከቫት በፊት ያለው ዋጋ መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በገዙት ጨረታ ሰነድ በሁሉም ገፅ ላይ የድርጅቱ ባለቤት ፊርማ፣ ሙሉ አድራሻውንና ሕጋዊ ማህተም ያረፈበት ኦርጅናሉን እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ በማድረግ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND) ለእያንዳንዱ ምድብ (ሎት) ከባንክ በተረጋገጠ CPO 10,000.00 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥራቸውን የሚገልጽ ሕጋዊ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን ከኮሌጁ የግዥ እና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር-4 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፤
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት ላይ የጨረታ ሣጥኑ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። በጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ሆኑ ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታ መክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ላይ ተዘግቶ የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን።
- ተጫራቾች አንድ ተጫራች የሰጠውን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት የተከለከለ ነው።
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡-0251-13 09 52/53/54/55
ፖስታ ሳጥን ቁጥር 2601
ፋክስ ቁጥር፡-0251-12 45 53 ማግኘት ይችላሉ።
ተጨማሪ ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ ባለው በዋጋ ማቅረቢያ ቦታ ላይ የሚሞሉት ዋጋ ከቫት በፊት መሆኑን እንዳይረሱት በድጋሚ ማሳሰብ እንፈልጋለን።
ኢትዮ- ጣሊያን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-09-22
- Bid closing time: 09:45
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ከጠዋቱ 3፡45 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-22 10:00
- Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Ethio-Italian Poly Technique College in Dire Dawa Administration
- Bid bond: 10,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 500.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Published on: Addis Zemen (Sep 04, 2026)
- Posted at: 2026-09-04T08:48:25.000Z