Equipment and Accessories
የአግአዚያን ቁ.2 ቅድመ አ/አ መካከለኛ /ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsComputer and Accessories
Addis Ababa
More tags
IT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesMaterialsEducation and TrainingCleaning and Janitorial Equipment and ServicePrinted Advertising MaterialsAdvertising and PromotionPrinting and PublishingTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsHand Tools and Workshop EquipmentOthersMaintenance and RepairHouse and BuildingHealth Related Services and MaterialsHealth Care, Medical IndustryMedical Equipment and SuppliesMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingConsumable GoodsStationeryOffice FurnitureFurniture and FurnishingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksConstruction Machinery and EquipmentAmharic2merkatoAgaziyan No.2 Kindergarten & Elementary School
Description
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2019 ዓ.ም.
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 08 የሚገኘው የአግዓዝያን ቁ.2 ቅድመ አ/አ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
- ልዩ ልዩ ቋሚ እቃዎች ፤
- አላቂ የትምህርት እቃዎች
- የፅዳት እና የቢሮ እቃዎች ፤
- ህትመት፤
- የደንብ ልብስ፤
- የጥገና እቃዎች፤
- የህንፃ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ ጥገና፤
- የህክምና እቃዎች፤
- የልማት እቃዎች፤ ሌሎች አላቂ እቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
- እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስVAፐተመዝጋቢ የሆኑናለዚህምየተመዘገቡበትን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 300(ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከአግ.ቁ.2 ቅድመ አ/አ/መካከለኛ/ደ/ት/ቤት/ፋይናንስ ክፍል 18 ቁጥር ቀርበው በተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች በገዙበት የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው።በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም ።
- ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት(VAT)ማካተት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል ።ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው ::
- የጨረታው አሸናፊ የሚለየው በሞላው ነጠላ /ጥቅል ዋጋ ሊሆን ይችላል።
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ሲያመጡ ደብዳቤው ላይ መፈረም ያለበት የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሀላፊ መሆን አለበት፣ የተደራጁበትን ዘርፍ ተጠቅሶ መፃፍ አለበት፣ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሰነድ መግዣ ዋጋ እና የውል ማስከበሪያ በነፃ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቅሶ መፃፍ አለበት።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 08 የሚገኘው የአግዓዝያን ቁ.2 ቅድመ አ/ አ/ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ሼል ዲፖ ፊት ለፊት ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ 100 ሜ ገባ ብሎ ። ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር ፡-011-470-76-58 / 011-442-80-51 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የአግአዚያን ቁ.2 ቅድመ አ/አ መካከለኛ /ደ / ት /ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-16
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን ከሰዓት 11፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-17 10:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Agaziyan No.2 Kindergarten & Elementary School
- Buyer address: ጎተራ ማሳለጫ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ሼል ዲፖ ፊት ለፊት ከሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ 50 ሜ ገባ ብሎ
- Bid bond: 10,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
- Posted at: 2026-09-05T09:16:30.000Z