Industrial Machinery Provision and Installation

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት የዳቦ ማሽን እና አክሰሰሪዎች፣ የኤክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የሠራተኛ ዳቦ ቤት አገልግሎት ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር 001/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን በ2/ሁለት/ሎች ማለትም፡-

  • ሎት 1 - የዳቦ ማሸን እና አክሰሰሪዎች፣
  • ሎት 2- የኤክትሮኒክስ፣ ዕቃዎች
  • ሎት 3 የሠራተኛ ዳቦ ቤት አገልግሎት፣

ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርት አሟልቶ በጨረታው መወዳደር ይችላል።

1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ ንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ያላቸው ፣ ግብር ከፋይነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት አቅራቢነት ማስረጃ ያለው፣ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ተመዝጋቢ የሆነ፣

 2. በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ አካል በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ

3. የጨረታ ማስከበሪያ፡- ለእያንዳንዱ ሎት ከአጠቃላይ ለበጀት ዓመቱ ከተበጀተው በጀት ከዐ.5-2% የተሰላ ነው

4. የባንክ አካውንት ያላቸው

ሎት 1

ሎት 2

ሎት 3

100,000.00

12,500.00

10,000.00

5. በእያንዳንድ ሎት ለብቻው በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ADDIS KETEMA SUB CITY ADMINSTRATOIN PUBLIC SERVICE & HUMAN RESOURECE DEVELOPMENT OFFICE PURCHASING ADMINISTRATION SUPPORTIVE PROCESS በሚል ስም የተሰራ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።

6. የሚታዘዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ተቀባይነት የሚኖረው የሲፒኦ ቁጥር የሚታይ ከሆነ፣ የተጫራቹን ስም በግልፅ የሚነበብ ከሆነ ሲፒኦ ጀርባ ላይ የባንኩ ማረጋገጫ ማህተም ያለው ከሆነ ብቻ ነው።

7. ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 አስር የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር / በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በሥራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 በአ/ከ/ክ/ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ለማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 መውሰድ ይችላሉ።

8. በከፍል 6 ባዶ በቴክኒክ መመዘኛዎች ላይ ተሟልቶ፣ ተፈርሞ እና ማህተም ተደርጎ፣ በሁሉም ገጽ ላይ ተፈርሞ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎ ሙሉ የጨረታ ሰነድ /መመሪያ ተመላሽ ይደረጋል

9. የጨረታ ሰነዱ ቴክኒካል ዋናውን አንድ/1/ እና ፎቶ ኮፒ/1/ ፋይናንሺያል ሰነድ ዋናውን አንድ /1/ እና ፎቶ ኮፒ አንድ/ 1/ለየብቻ በፖስታ ታሽጎ በድምሩ አራት⁄4/ ፖስታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ኦርጅናል(ኮፒ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል በሚል በፖስታው ላይ በመግለጽ በፃፍ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን አ/ከ/ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ለማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይኖርበታል።

10. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት እና ፖስታውን ለማስገባት ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ በአዲስ ከተማ ከ/ከተማ አስተዳደር ፐብሊ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605 ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡00 የጨረታው ሳጥን የሚታሸግ ሲሆን በዚሁ ቀን ጠዋቱ 3፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፤ ነገር ግን 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።

11. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡።

ለተጨማሪ መረጃ ፡- 011-827-9979 / 011-895-9223 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፤

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ ክፍስ ከተማ አስተዳደር ከገሩም ሆስፒታል ከፍ ብሱ በአዲስ

ከተማ ክፍስ ከተማ ፐብሲክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን፤

6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 605

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ  ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-16
  • Bid closing time: 17:30
  • Bid closing (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 09:00
  • Bid opening (note): ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T09:44:13.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders