Equipment and Accessories

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ከዚህ በታች ያሉትን እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዢያ በባንክ የተረጋገጠ cpo በየሎቱ

  1. ሎት1 አላቂ የቢሮ እቃዎች 9000 (ዘጠኝ ሺ ብር)
  2. ሎት2 የጽዳት፣ የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ ዕቃዎች  8000 (ስምንት ሺህ ብር)
  3. ሎት3 ቋሚ ዕቃዎች 8000 (ስምንት ሺ ብር)
  4. ሎት4 የኤሌትሮኒክስ ዕቃዎች 8000 (ስምንት ሺህ ብር)
  5. ሎት5 የጥገና ሥራዎች  3000 (ሶስት ሺህ ብር)
  6. ሎት6 የመኪና እና የሞተር ጎማዎች 5000 (አምስት ሺህ ብር)
  7. ሎት7 መስተንግዶ ግዥ  3000 (ሶስት ሺህ ብር)
  8. ሎት8 አዳራሽ ዲኮር የወንበር ዲኮር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
  9. ሎት9 የህትመት ስራዎች  3000 (ሶስት ሺ ብር)
  10. ሎት10 የትራንስፖርት /መጓጓዣ  500 (አምስት መቶ ብር)
  11. ሎት 11 ዘር /አዝዕርት  1000 (አንድ ሺህ ብር)

ብቃት ያላቸዉንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳደሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል በዚህ መሰረት

1. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስት ግ/ን/አስ/ኤጀንሲ ድህረ ገፅ ላይ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ፤ ቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው

3. ተጫራቾች ጨረታው በአድስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል በቀድሞው ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በአሁኑ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 501 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት በፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 501 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛ ቀን በ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 4:30 ሰዓት በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 501 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት 1፣ ሎት 2 እና ሎት 7 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለሎት 3፣ ለሎት 4 እና ለሎት 5 በቀረበው እስፔስፕኬሽን መሰረት የተሟላ እስፔስፕኬሽን ማዘጋጀት እና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

7. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።

8. የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

9. አሽናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

10. የጨረታ አሸናፊ እንደሆኑ ከተለየ ቦሃላ አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐረሰንት ውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረ ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ сро ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

አድራሻ አዲስ አበባ በቀድሞው ን/ስ/ላ/ክ/ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር በአሁኑ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አስተዳደር ከሳር ቤት ወረድ ብሎ ሀረር ክሊኒክ ፊት ለፊት 300 ሜትር ገባ ብሎ የመስሪያ ቤቱ ስልክ ቁጥር 011 383 4260
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛ ቀን በ 4:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛ ቀን በ 4:30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lideta Sub City Wereda 04 Administration Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Lessan (Sep 05, 2026)
  • Posted at: 2026-09-05T10:08:38.000Z
← Back to all tenders