Equipment and Accessories
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በወረዳ ሁለት የሚገኘው የአቢሲኒያ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
ግልጽ ጨረታ ቁጥር 001/2019
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት በወረዳ ሁለት የሚገኘው የአቢሲኒያ ጤና ጣቢያ ለ2019 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎት1፡- ኤሌክትሮኒክስ፣ ኤሌክትሪሲቲ ዕቃዎች ሎት 2፡- የተለያዩ የቢሮ መገልገያ እቃዎች ሎት 3፡- የጽዳት ዕቃዎች ሎት፡-4 ልዩ ልዩ የሕትመት ሥራዎች ሎት 5 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች ሎት 6፡- የሠራተኛ የደንብ ልብስ እና ብትን ጨርቆች እና ልዩ ልዩ የልብስ ስፌት ሥራዎች 7. የተለያዩ የጥገና ዓይነቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ሰነድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። የአቅራቢነት ሊስት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የምናረጋግጥ ይሆናል። www.pp.agot ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስር ተከታታይ የሥራ ቀናት ወረዳ ሶስት አቢሲኒያ ጤና ጣቢያ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 407 በመቅረብ ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የተጫረቱበትን ዋጋ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ዝርዝር ከነቫቱ ሞስተው ያስገባሉ። ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር በየሎቱ ሎት1.5000(1%) ሎት 2 7500(1.5%) ሎት 3. 4000(0.75) ሎት 4. 3500(0.75) ሎት 5 4000(0.75) ሎት6 5000(1%) ሎት 7.5000(1%) በባንክ በተመሰከረለትየክፍያ ትእዘዘ (ሲፒኦ) ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራቾች ለሚያቀርቡት ዕቃ ናሙና የማቅረቢያ ጊዜ ጨረታው ከመከፈቱ አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ሲቀሩት ብቻ ነው፡፡ ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት በጤና ጣቢያው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0112 735 575 / 0112 735 126 / 0112 734 227
አድራሻ፡- ድሬ ሕንፃ አጠገብ ካለው ቢንዚን ማደያ በስተጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል፡፡
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት አቢሲኒያ ጤና ጣቢያ
Tender details
- Deadline: 2026-09-18
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-18 12:00
- Bid opening (note): ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Abisiniya Health Post
- Buyer address: ድሬ ሕንፃ አጠገብ ካለው ቤንዚን ማደያ በስተጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 06, 2026)
- Posted at: 2026-09-07T08:40:51.000Z
- Source: 2merkato