Vehicle and Machinery Sale

አንበሳ ባንክ አ.ማ. አውቶሞቢል (ሀዩንዳይ ኤሌንትራ) በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

አንበሳ ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2012 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተጠቀሰውን ንብረት በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪ ስም

ንብረት አስያዥ ስም

አበዳሪ ቅርንጫፍ

የመኪና ዓይነት የሰሌዳ ቁጥር የሻንሲ ቁጥርና የሞተር ቁጥር

የጨረታ መነሻ ዋጋ

ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ ቀን እና ሰዓት

የሰሌዳ ቁጥር

የመኪናው አይነት

የሞተር ቁጥር

የሻንሲ ቁጥር

የስሪት ዘመን

2

አቶ ሰለሞን ዮሃንስ ገሰሰው

አቶ ሰለሞን ዮሃንስ ገሰሰው

ሳር ቤት

02-A92960አአ

አውቶሞቢል (ሀዩንዳይ ኤሌንትራ)

G4FGGU007160

KMHD841C BGU322492

2016

2,800,000.00

ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት መስከረም 13 ቀን 2019 . ከጠዋቱ 400-600 ድረስ ይሆናል::

1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

2. ጨረታ የሚካሄደው 22 አካባቢ በሚገኘው ሌክስ ፕላዛ ሕንፃ ላይ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ይሆናል።

3. የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው ከ4፡00 - 5:30 ድረስ ይሆናል፡፡ ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ሰዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።

4. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል፡፡

5. የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።

6. የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል::

7. ለጨረታ የቀረበውን ንብረት ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል::

8. በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው:: ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን፡፡

9. ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል፡፡

10. ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊትም ሆነ በኋላ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው ተ.እ.ታን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም የግብር ክፍያዎች እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ የአሹራ፣ የስም ማዘዋወሪያ ክፍያዎችን ጨምሮ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሸናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።

11. ባንኩ ከጨረታ በፊት እና በኋላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት እና ሪከቨሪ ጽ/ቤት በስልክ ቁጥር 011-662-7120 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።


Tender details

  • Deadline: 2026-09-23
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid opening: 2026-09-23 12:00
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Lion International Bank S.C.
  • Bid bond: 25%
  • Published on: Reporter (Sep 06, 2026)
  • Posted at: 2026-09-07T11:48:29.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders
Could not load content