Equipment and Accessories
የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 የበጀት ዓመት ማዕከሉ ለሚየመርታቸው የምርምር ዕቃዎችና ቴክኖሎጂዎች ግብዓት የሚውሉ ብረታ ብረቶች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ለወርክ ሾፕ ሥራ የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣ በአጠቀላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
More tags
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ለ2019 የበጀት ዓመት ማዕከሉ ለሚየመርታቸው የምርምር ዕቃዎችና ቴክኖሎጂዎች ግብዓት የሚውሉ ብረታ ብረቶች የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ለወርክ ሾፕ ሥራ የሚውሉ ቋሚ እና አላቂ ዕቃዎች፣ በአጠቀላይ ለምርምር ሥራ የሚውሉ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘርዘሩትን መስፈርቶች ሊኖረው ይገባል።
1. ለሚጠየቁ የግዥ እቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፣ የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፍቃዳቸውን ያሳደሱና ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለቸውና በፌደራል ወይም በክልል ገንዘብና እኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት /Suppliers list/ ያላቸውና የተመዘገቡበትን የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን እንዲሁም የግባር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax Payer Registration No) ቲን ነምበር ዋናውን እና ኮፒውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው መ/ቤት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ሰነድ የማይመለስ 1,000.00 ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
4. ተጫረቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አሰላ በሚገኘው የማዕከሉ ጽ/ቤት ድረስ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት፣ ካልተገኙም በሌሉበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡45 ሰዓት በአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል ቢሮ ቁጥር 24 ይከፈታል።
5. ተጫረቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 ታዋቂ በሆነ ባንክ በ “CPO” ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ማዕከሉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- በስልክ ቁጥር 0223311861 /0223312492/0930509164/09 12263915 ደውሎ መጠየቅ ይቻለል።
የአሰላ ግብርና ምህንድስና ምርምር ማዕከል
Tender details
- Deadline: 2026-09-24
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-24 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡45 ሰዓት
- Region: Oromia
- Publishing entity: Assela Agricultural Engineering Research Center(AAERC)
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
- Posted at: 2026-09-08T08:43:14.000Z
- Source: 2merkato