Equipment and Accessories

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ)፣ የመኪና ጎማ፣ የፅህፈት መሳሪያዎች፣ የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎችንና ደንብ ልብስ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት በሥሩ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች

  • ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ኤሌክትሮኒክስ)፤
  • የመኪና ጎማ፤
  • የፅህፈት መሳሪያዎች
  • የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎችንና
  • ደንብ ልብስ አቅራቢ ድርጅቶችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

  1. ተጫራቾች በየንግድ መስኩ ህጋዊ የሆነና የተደሰ ንግድ ፍቃዳቸውን ፣ዓመታዊ የሥራግብር የከፈሉበትን፣በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን የሚገልፅ መረጃ ሰነዶቻቸውን ፎቶኮፒውን ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 500(አምስት መቶ) በመከፈል ከዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ከፍል በመቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለቋሚ ዕቃዎች(ኤሌክትሮኒክስ) 100,000 (አንድ መቶ ሺህ)ብር ፤ ለጎማ 100,000 (አንድ መቶ ሺህ)ብር፤ ለፅህፈት መሳሪያዎች፤ የፅዳትና ቋሚ አላቂ ዕቃዎች 100,000 (አንድ መቶ ሺህ)ብር እንድሁም ዳንብ ልብስ 50,000 (ሀምሳ ሺህ) ብር በዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ሥም በባንክ የተመሰከረለት (CPO) ከጨረታው ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ በግልጽ በመጻፍ ኮፒ ና ኦሪጅናሉን በመለየት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለበት።
  5. ጨረታው የሚከፈታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን፤ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ7፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውና ታዛቢዎች በተገኙበት በዞኑ ገንዘብ ጽ/ቤት ይከፈታል።
  6.  የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በፅሁፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ10 ቀን ውስጥ የጨረታ ውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላለ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ቢዲቦንድ (Bid Bond) በማስያዝ ከመስሪያቤቱ ጋር መፈራረም አለበት።
  7. አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊዎች ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
  8. ያሸነፉትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ መ/ቤቱ ግምጃ ቤት ማምጣት የሚችል።
  9. መ/ቤቱ የተሸለ አመራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

ስልክ ቁጥር: +251911113565/+251919098861/+251913063862/+251936532376

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-25
  • Bid closing time: 11:30
  • Bid closing (note): ጨረታው የሚከፈታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን፤ ከቀኑ 5፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-25 13:30
  • Bid opening (note): ጨረታው የሚከፈታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን፤ ከቀኑ 7፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የምዕራብ ጉጂ ዞን ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 08, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T08:50:07.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders