Equipment and Accessories

የካ ጣፎ የመጀ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2019

የካ ጣፎ የመጀ/ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

እነርሱም፡-

  • የቴክኖሎጂ ዕቃዎች፣
  • አላቂ የቢሮ ዕቃዎች እና ኣላቂ የት/ት ዕቃዎች፣
  • የፅዳት ዕቃዎች፣
  • የሠራተኛ የደንብ ልብስ፣
  • የሕትመት፣
  • ፈርኒቸር፣
  • የኮምፒውተር ጥገና፣ ሕንፃ መሣሪያ ግዢን እንዲሁም ልዩ ልዩ ግዥን ይመለከታል።
  1. ተጫራቾች ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ እንዲሁም የአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ ለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00/ ሁለት መቶ ብር ለእያንዳንዱ ሎት በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ብቻ በየካ ጣፎ የመጀ/ደ/ት/ቤት ፋይናንስ ግዢ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ፤ ምዝገባ ወረቀትና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO. /ማቅረብና VAፐ(ቫት) ከፋይ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ተመላሽ የሚሆን ብር በባንክ በተመሰከረለት የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ሎት1- 10,000ብር - ሎት 2- 5,000ብር ሎት 3 5,000ብር -ሎት4- 5,000ብር ሎት-5 10,000ብር ሎት 6 -10,000ብር -ሎት -7- 5,000ብር ሎት-8-10,000ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. ተጫራቾች ጨረታውን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ ቀኑ 10፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ እና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  6. ተጫራቾች ከዋናው ሰነድ በተጨማሪ ፋይናንሽያል እና ቴክኒካል ሰነዳቸውን ኮፒውን እና ኦርጂናሉን ማስገባት አለባቸው።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ ማሸግ እና ላዩ ላይ የድርጅቱን  ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  8. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ እቃ ነጠላ ዋጋ በቀረበው ሰነድ ላይ 15% ቫትን ጨምረው መሙላት ይኖርባቸዋል።
  9. የጨረታው አሸናፊዎች ማሸነፋቸው በጽሑፍ የሚገለጽላቸው ሲሆን ለጨረታ አፈፃፀም ውል ማስከበሪያ ላሸነፉበት ዕቃ ዋጋ 10% በታወቀ ባንክና በተመሰከረለት ሲፒኦ በማስያዝና ውል የማዋዋል ግዴታ አለባቸው።
  10. የጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ ደብዳቤ የምታጽፉ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች የተሰማራችሁበትን የንግድ ሥራ መስክ/ ዘርፍ/ የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡ እንዲሁም የፈጠራና ክህሎት ሚኒስቴር ደረጃቸው መሆኑና በሚያመርቱት ምርት ብቻ እንዲወዳደሩ እናስታውቃለን።
  11. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ ስትመልሱ ሙሉ አድራሻችሁን በተሰጠው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በትክክል መሙላት ይኖርባችኋል።
  12. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊልም የመሰረዝ መብት አለው።
  13. ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ለ45 ቀናት ብቻ ነው።
  14. በጨረታ ሰነድ የቀረበው የዕቃ ብዛት ት/ቤቱ 25% መጨመርና መቀነስ ይችላል።
  15. ተጫራቾች ተወዳድረው ካሸነፉ በኋላ ከናሙናው ምንም አይነት ለውጥ ሳያደርጉ በራሳቸው ወጪ ጭነው ማቅረብና ደረጃውን ያልጠበቀ ዕቃ ከሆነ መልሰው ትክክለኛውን በቀረበው ናሙና መሠረት ማምጣት ግዴታ አለባቸው።
  16. ተጫራቾች ጨረታውን ሲያስገቡ ለእያንዳንዱ እቃዎች ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  17. በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይከፈታል።

ልዩ ቦታው ከአያት ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከገ/ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎይገኛል።

የካ ጣፎ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-09-18
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-18 10:30
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Yeka Tafo Kindergarten and Primary School
  • Buyer address: ከአያት ወደ ጣፎ በሚወስደው መንገድ ከገ/ቤተክርስቲያን አለፍ ብሎ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T09:26:10.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders