Products and Services

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ የምግብ እህል አቅርቦት (ድፍን ጥሬ አተር) እና የግንባታ ብረት ውጤቶች አቅርቦት (የጣርያ ኬንች ቲቦላሪ ብረት RHS) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር 05/2019 ዓ/ም

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ

  • ሎት1. የምግብ እህል አቅርቦት( ድፍን ጥሬ አተር)፣
  • ሎት2. የግንባታ ብረት ውጤቶች አቅርቦት (የጣርያ ኬንች ቲቦላሪ ብረት RHS) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

 ስለሆነም መወዳደር የምትፈልጉ የሚከተሉትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ከሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርኘራይዝ ስራ ክፍል በመዉሰድ ዋጋ በመሙላት የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ የድርጅቱን ስምና ማህተም በማድረግ ፖስታ በማሸግ ከጨረታ መዝጊያ ቀን በፊት በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን በኢንተርኘራይዙ ቢሮ ቁጥር 001 የጨረታ የሰነዱን ዋጋ በመሙላት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ ከሆኑ ተመዝጋቢ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸዉ፡፡ የሚገዛዉ ዕቃ ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ የሚሆን ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ አቅራቢ ድርጅቶች ብቻ የሚወዳደሩ ሆነው ለሚገዛው እቃ በኪው አር በታተመ ደረሰኝ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲመልሱ ለሎት1 የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) ፣ ለሎት 2. የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 100,000 (አንድ መቶ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. የጨረታው አሸናፊ የዉል ማስከበሪያ ገንዘብ 10 በመቶ በጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በመክፈል ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታ ሰነዱ ማስገባት የሚጀምረዉ ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ሲሆን ጨረታዉ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዚያዉ ቀን በ ከረፋዱ 4:30 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መከፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል:: ነገር ግን የጨረታ መክፈቻ ሰዓት አቅራቢዎች ወይም ወኪሎች ባይገኙም ለጨረታ አከፋፈት ስርዓቱ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  7. አሸናፊዉ ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ከ7 ቀን በኋላ ባሉት 8 ቀናት ዉስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
  8. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  9. አሸናፊዉ ድርጅት በግዥ መመሪያው መሰረት የቅድመ ግብር ሶስት በመቶ እንደሚቆረጥበት ታሳቢ ተደርጎ ዋጋውን መሙሉት ይኖርበታል፡፡
  10. ኢንተርፕራይዙ ባወጣው ጨረታ ላይ 50 በመቶ የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
  11. አድራሻ በአዊ አስ/ዞን እንጅባራ ከተማ እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ነዉ፡፡
  12. ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 42 26 44 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-17 10:30
  • Bid opening (note): ማስታወቂያዉ በጋዜጣ ከወጣበት ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ11 ኛዉ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: ሱታና ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
  • Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T13:29:03.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders