Equipment and Accessories

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በካፒታል በጀት ለሶላር ሲስተም የሚያገለግሉ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-001/2019

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ በካፒታል በጀት ለሶላር ሲስተም የሚያገለግሉ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቾች የሚያሟሉ መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
  2.  የግዥው መጠን በየንግድ ዘርፉ ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3.  ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  4. የሚገዙ የዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 50,000 (ሀምሳ ሽህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6.  በጨረታው ፍላጎት ያላቸው ህጋዊ ድርጅቶች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ቢሮ ቁጥር 23 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነድ መግዛት የሚቻል ሲሆን ተጫራቾች ለመወዳደር የመወዳደሪያ ሰነዶችን ሲመልሱ የድርጅቱ ህጋዊ ማህተም፣ ፊርማ እና አድራሻ በትክክል በመሙላት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካልና ፋይናንሽያል በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  7.  ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም የተወሰደው እርምጃ በማስረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፡፡
  9.  የማቅረቢያ ጊዜ ውል ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10 ቀናት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ርክክብ የሚፈ,ፀም ይሆናል፡፡ ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
  10.  መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11. ስለጨረታ ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 01 32 /058 220 10 87 ዘወትር በስራ ቀናት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
    አድራሻ የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ ወይም ቀበሌ 07 ባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ዊዝደም ፊት ለፊት ይገኛል፡፡

የአብክመ ውሀና ኢነርጂ ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-17
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን 8፡00
  • Bid opening: 2026-09-17 14:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን 8፡30
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara Regional State Water and Energy Bureau
  • Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
  • Bid document price: 200 (ሁለት መቶ ብር)
  • Published on: Be'kur (Sep 07, 2026)
  • Posted at: 2026-09-08T13:57:08.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders