Equipment and Accessories

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በ2019 ዓ.ም. የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እና የመኪና እቃ መለዋወጫ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ቁጥር፡ ገቢዎች ቢሮ/ቢ/ግ/ጨ/01/2019

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገቢዎች ቢሮ በ2019 ዓ.ም ከተፈቀደለት በጀት ላይ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  1. ሎት-1. የፈርኒቸር ዕቃዎች
  2. ሎት-2. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች
  3. ሎት-3. የመኪና እቃ መለዋወጫ

ሆኖም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

1.ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብና ኦሪጅናል በአንድ ፖስታ ኮፒውን ደግሞ በሌላ ፖስታ በማድረግ እንዲሁም የተጫራቾች ስምና ፊርማ እና አድራሻ እንዲሁም የሎት ቁጥር እና የሎት ስም በሁለቱም ፖስታዎች ላይ በግልጽ የተጻፈበትን በአንድ ታላቅ ፖስታ አድርገው በስም ታሽጎ ከዚህ በጨረታ ማስታወቂያ በተወሰነው ጊዜና ሰዓት በአፋር ብ/ክ/መ/ ገቢዎች ቢሮ በግዥና ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ማስገባት አለባቸው።

2. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብ ቢሮው ለመግዛት የፈለገውን የፈርኒቸር ዕቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች እና የመኪና እቃ መለዋወጫ ሲሆኑ ስራው ለሰነዶች የተወዳዳሪዎች የሚሆኑ ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ለኢኮኖሚያቸው ኦሪጅናል እና ኮፒ ሰነድ የማያያዝ ግዴታ አለባቸው።

3. የሚገዙት እቃዎች አይነት እና ዝርዝር መግለጫ (Specification) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

4.ተጫራቾች ግዥው መንግስት መስሪያ ቤት ያቀረበላቸውን የመወዳደሪያ መስፈርቶች አሟልተው ከቀረቡ በሶስቱም ሎቶች የመወዳደርና አሸናፊ መሆንም ይችላሉ።

5. ተጫራቾች በአንድ ከፈለጉም በሁለቱም ሎቶች መሳተፍ ይችላሉ። ሰስቱም

6. በሁሉም ሎቶች የሚወዳደር ተጫራች የእያንዳንዱ ሎት የተለየ ፖስታ በውስጡ ኦሪጅናል እና ኮፒ የሚሉ ሌሎች ፖስታዎች መያዝ ያለበት ሲሆን የሶስቱም ሎቶች ሰነዶችም ተሰብስበው በአንድ ትልቅ ፖስታ ሆነው መቅረብ አለባቸው።

7. ማንኛውም የጨረታ ተወዳዳሪ ለሚያቀርባቸው ዕቃዎች ለየብቻ ማለትም ለሎት አንድ (1) 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ)፤ ለሎት ሁለት (2) 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) ለሎት 3 25,000.00 (ሀያ አምስት ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ በሲ ፒኦ (CPO) ከመወዳደሪያ ሃሳብ ማቅረቢያ ጋር በፖስታ ታሽጎ መቅረብ አለበት።

8. ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘ የእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 1,000.00 ብር (አንድ ሺህ ብር ብቻ) ከፍለው ከአፋር ብ/ክ/መ/ገቢዎች ቢሮ በግዥ/ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 06 በግንባር ቀርበው መውሰድ ይቻላል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሽያጭ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በአስረኛው ቀን እስከ ቀኑ 9:30 ድረስ ብቻ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ሞልተው ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው።

10.  ጨረታው በአስረኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአፋር ብ/ክ/መ/ ገቢዎች ቢሮ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

11. የፈርኒቸር ዕቃዎች የሚያቀርበው አሸናፊ ድርጅት የፈርኒቸር ዕቃዎች በአፋር ብ/ክ/መንግስት በሰመራ ከተማ በራሳቸው ወጪ አምጥተው በራሳቸው ወጪ የማስጠገን ግዴታ አለባቸው።

12. አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉበትን እቃዎች አፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ ድረስ ወጪውን ሸፍኖ የማቅረብ ግዴታ አለበት።

13.የጨረታ መክፈቻ ፕሮግራም በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙ የጨረታው መክፈቻ ስነ ስርዓት አያስተጓጉለውም።

14.ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

15. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፦ 0921 333 838 ወይም በኢሜል [email protected]  በስልክ ደውለው ወይም በጽሁፍ መጠየቅ ይችላሉ።

የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገቢዎች ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-19
  • Bid closing time: 15:30
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን እስከ ቀኑ 9:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-19 16:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 10:00 ሰዓት
  • Region: Afar
  • Publishing entity: Afar Bureau of Revenue
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
  • Published on: Addis Zemen (Sep 09, 2026)
  • Posted at: 2026-09-09T09:01:05.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders