Equipment and Accessories
የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ቋሚ እቃዎች፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፤ የፅዳት እቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የጥገና እቃዎች፣ ቤተ መጻህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Equipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsOffice Furniture
Addis Ababa
More tags
Furniture and FurnishingHouse FurnitureComputer and AccessoriesIT and TelecomOffice Machines and AccessoriesOffice Supplies and ServicesMaterialsEducation and TrainingCleaning and Janitorial Equipment and ServiceTextile, Garments and UniformsTextile, Garment and LeatherShoes and Other Leather ProductsStationeryOthersMaintenance and RepairAmharic2merkatoAddis Amba Kindergarten and Elementary School
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን
- ቋሚ እቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ እቃዎች፣
- አላቂ የትምህርት እቃዎች፤
- የፅዳት እቃዎች፣
- የደንብ ልብስ፣
- የጥገና እቃዎች፤
- ቤተ መጻህፍት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች በዝርዝር የቀረቡትን መስፈርት የምታሟሉ ተጫራቾች በሙሉ በጨረታው እንድትሳተፉ እንጋብዛለን።
- እቃውን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችል ብቃት፤ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ኮፒ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚህም የተመዘገቡበትን ኮፒ አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር ብቻ) በመክፈል ሰነዱን ከአዲስ አምባ የመ/ደ/ት/ቤት/ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 05 ክፍል ቀርበው በ 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ተጫራቾች በገዙበት የጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ ዝርዝር መሙያ ላይ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። በሌላ ሰነድ ከሞሉ ተቀባይነት የለውም።
- ባቀረቡት ዋጋ ዝርዝር ላይ ቫት (VAT) ማካተት አለባቸው።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል ይከፈታል። ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የሚጫረቱበትን የመወዳደሪያ ዋጋ ሞልተው በታሸገ ፖስታ ውስጥ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።
- ከጥቃቅን እና አነስተኛ ደብዳቤ ይዘው የሚመጡ ተጫራቾች ካደራጃቸው አካል ደብዳቤ ሲያመጡ የተደራጁበትን ዘርፍ ተጠቅሶ ቀጥታ በት/ቤቱስም ማፃፍ አለበት። የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) የሰነድ መግዣ ዋጋ እና የውል ማስከበሪያ በነፃ መውሰድ እንደሚችሉ ተጠቅሶ መፃፍ አለበት።
- ትምህርት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የሚገኘው የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አዲስ ሰፈር ድልድይ ወረድ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ፊት ለፊት።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-442-0441 / 011-470-7017 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 09 የአዲስ አምባ አፀደ ህፃናትና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-09-23
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው የሥራ ቀን አየር ላይ ውሎ በ10ኛው ቀን 11 ሰዓት
- Bid opening: 2026-09-24 10:00
- Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ በ 4 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Amba Kindergarten and Elementary School
- Buyer address: ን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 09 አዲስ ሰፈር ድልድይ ወደ ኪዳነምህርት ቤተ-ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ አዲስ ሰፈር ጣና ገበያ ማዕከል ፊት ለፊት
- Bid bond: 15,000.00 ብር
- Bid document price: 150.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 12, 2026)
- Posted at: 2026-09-12T09:37:04.000Z
- Source: 2merkato