Equipment and Accessories

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም የደንብ ልብስ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ መመሪያ

በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 ዓ/ም በጀት በወረደው ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች

  • ቋሚ እና አላቂ የቢሮ ዕቃዎችን እንዲሁም
  • የደንብ ልብስ ለመግዛት

 የወጣ የጨረታ ደንብ እና መመሪያ እንደሚከተለው ተዘርዝሯል።

  1. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የ2018 የመንግስት ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም /ቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  3. በ/ገ/አ/ት/ሚንስቴር ባቅራቢዎች የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን የሚፈልጉት ዕቃ በምን በምን አይነት እቃዎች ላይ መሆኑን ለይተው መግለፅ አለባቸው።
  5. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኃላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፁትን ማንኛውንም ሁኔታዎችን መለወጥ ወይም ማሻሻል ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይቻልም።
  6. መስሪያ ቤቱ የሚገዛውን እቃዎች ብዛት እንደአስፈላጊነታቸው በሙሉ ወይም በከፊል ማዘዝ ይችላል።
  7. የሚቀርቡት እቃዎች በተሰጠው እስፕስፊኬሽን ካልቀረቡና ማንኛውም አይነት ስህተት ቢፈፀም ሃላፊነቱ የአቅራቢው ይሆናል።
  8. ጨረታው የሚካሄደው የድርጅቱን የገብያ ጥናት ማእከል የማድረግ ሲሆን ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት እቃዎች አይነት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቹ ያንዱን ዕቃ ዋጋ በቁጥርና በፊደል መፃፍ አለበት። በቁጥርና በፊደል በተፃፈ መካከል ልዩነት ቢኖር በፊደል የተጻፈው ይወሰዳል።
  9. አቅራቢው ድርጅት እቃዎችን ቄለም ወለጋ ዞን በየማሎሚ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት መጋዝን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ አለባቸው።
  10. ተጫራቾች ላሸነፉባቸው እቃዎች ከመስሪያቤቱ ጋር ውል መግባት አለባቸው።
  11. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አሥር ሺህ) ብር ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርበታል።
  12. አሸናፊዎች በሚገቡት ውል መሰረት ለመፈጸም ለውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ለውል ማስከበሪያ የተያዘ ሲፒኦ በውሉ መሰረት እስኪፈጸም ተይዞ ይቆያል።
  13. ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለውል ስምምነት ያስያዙት ገንዘብ ለመስሪያ ቤቱ ገቢ ይሆናል።
  14. ተጫራቾች በሰነዳቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን ገልጸው መፈረም አለባቸው።
  15. የሚቀርበው ሰነድ ስሪዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ የሚታይ መሆን አለበት።
  16. ከተጠየቀው ብዛት አሳንሶ ማቅረብ አይቻልም።
  17. ተጫራቾች ከጨረታው መክፈቻ እለት ጀምሮ ያቀረቡት ዋጋ የሚቆይበት ጊዜ አጠናቀው validity date/እቃውን የሚያስገቡበትን ቀን መግለፅ አለባቸው።
  18. አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  19. ተጫራቾች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል።
  20. ተጫራቾች ከሽያጭ በኃላ የሚሰጡት አገልግሎት/after sales service/ መግለፅ ይኖርባቸዋል።
  21. ዋጋው መሞላት ያለበት መ/ቤቱ ባዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ነው።
  22. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዝሁ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  23. በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የጨረታ ሰነድ በማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) ከየማሎጊ ወለል ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት መግዛት ይችላል።
  24. ተጫራቾች የቴክኒክና የዋጋ ፖስታ እንድሁም ኮፒ ለየብቻ ወይም በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማሸግ አራቱን በአንድ ላይ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
  25. ማንኛውም ተጫራች የሚያቀርበው ዋጋ ቫትን ጨምሮ ማቅረብ አለበት፡፡ወይም የሚያቀርበው ዋጋው ከቫት ጋር መሆን አለበት።
  26. ማንኛውም ተጫራች መ/ቤቱ የፈለጋቸውን ዕቃ ያንዱን ዋጋ መሙላት አለበት። ሞልቶ  ካልተገኘ የሌላ ተጫራች ትልቁ ዋጋ ይደመርበታል። ጨረታው የሚገመገመው የመ/ቤቱ የገበያ ጥናትን ማዕከል ያደረገ ሲሆን ከገበያ ጥናቱ 10 ከፍ ያለ ዋጋ ወይንም ዝቅ ያለ ዋጋ ውድቅ ይደረግና የገበያው የዕቃው የተጠና ዋጋ ይደመርበታል።
  27. በቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጆ ከተማ የጨረታው ሰነድ ስለሚገኝ መጥቶ መግዛት ይቻላል።

ማሳሰቢያ፡ የመ/ቤታችን የግዥ መጠን በ20/% መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል።

መ/ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

ለተጨማሪ መረጃ

አድራሻ፡- ቄለም ወለጋዞን የማሎጊ ወለል ገ/ኢ/ት/ጽ/ቤት ተጆ

ስልክቁጥር፡- 09 10 31 08 20 / 09 17 36 90 84

ተጫራቾች መሸነፋቸው እንደተረጋገጠ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያው ይመለስላቸዋል።

ቄለም ወለጋ ዞን የየማሎጊ ወለል ወረዳ

ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-10-08
  • Bid closing time: 17:00
  • Bid closing (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዝሁ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ
  • Bid opening: 2026-10-09 08:30
  • Bid opening (note): ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ 21 ተከታታይ ቀናቶች አየር ላይ ውሎ በዝሁ ቀን በ11፡00 ሰዓት ተዘግቶ በማግስቱ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Kellem Wollega Zone Yemalogi Welel Woreda FEDB
  • Bid bond: 10,000.00 ብር
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T08:56:45.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders