Equipment and Accessories

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የተለያዩ እቃዎች ግዥ ለ2019 ዓ.ም. በጀት ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር ጀዊ/001/2019 ዓ.ም

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ለተለያዩ ዲፓርትመንቶች የስልጠና ግብዓቶች አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች የአይሲቲ እና አላቂ AR/R Simulation system የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች የደንብ ልብስ የጽዳት ዕቃዎች የጽህፈት መሳሪያ ዕቃዎች የተለያዩ መድሃኒቶች እና የክኒኒክ ቋሚ ዕቃዎች የቢሮ መጋረጃ እና ምንጣፍ የከብቶች መኖ ግዥ 1ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ለ2019 ዓ.ም በጀት ዓመት ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት፦

  1. ሎት 1 Augment Reality virtual reality or AR/R Simulation System
  2. ሎት 2 የICT አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች እና
  3. ሎት 3 የኮንስትራክሽን አላቂ እና ቋሚ እቃዎች
  4. ሎት 4 የብረታ ብረት አላቂ እና ቋሚ እቃዎች
  5. ሎት 5 የውድወርክ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች
  6. ሎት 6 የኤሌክትሪሲቲ ኤሌክትሮኒክስ አላቂ እቃ ቋሚ እቃዎች
  7. ሎት 7 የአውቶሞቲቭ አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች
  8. ሎት 8 የከተማ ግብርና አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች
  9. ሎት 9 ፊዚኮ ኬሚካል አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች
  10. ሎት 10 የሆቴልና ቱሪዝም ፀጉርና ውበት አላቂ እና ቋሚ ዕቃዎች
  11. ሎት 1 የቢሮ ፈርኒቸር ዕቃዎች
  12. ሎት 12 የሰርቬይንግ ማሽነሪ ዕቃዎች
  13. ሎት 13 የቢሮ መጋረጃ እና ምንጣፍ
  14. ሎት 14 የፅህፈት መሳሪያ ዕቃዎች
  15. ሎት 15 የደንብ ልብስ
  16. ሎት 16 የፅዳት ዕቃዎች
  17. ሎት 17 የከብቶች መኖ
  18. ሎት 18 የህትመት ስራ
  19. 1ሎት 19 የተለያዩ መድሃኒቶች እና ለክኒኒክ የሚያስፈልጉ ዕቃዎች

ማንኛውም ተወዳዳሪ

  • በዚሁ ዘርፍ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ
  • የግብረ ከፋይ TIN ሰርተፍኬት
  • የቫት (VAT) ተመዝጋቢ
  • በመንግስት ግዢ መሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢነት (Supplier list) የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

1. በተጠየቀው ዝርዝር እስፔስፊኬሽንና መለኪያ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል የሚያቀርቡት ዋጋ 15%ቫት ማካተትና ዋጋም ሲሞሉ ኮሌጁ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

2. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረተው እቃ ናሙና እንዲያቀርቡ በተጠየቀባቸው እቃዎች አስቀድሞ ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የተጠየቀውን ናሙና ወይም ሳምፕል ማቅረብ አለባቸው።

3. ከላይ ለተገለፁት ሎቶች 

  • ለሎት 1 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ ብር)
  • ለሎት 2 = 250,000 /ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/
  • ከሎት 3 እስከ ሎት 12 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
  • ከሎት 13 እስከ ሎት 16 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር)
  • ከሎት 17 እስከ ሎት 19 ድረስ ለእያንዳንዱ ሎት 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ ለሁሉም ሎቶች በጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም CPO በማሰራት ማስያዝ አለባቸው።

4. ከላይ ለተዘረዘሩት ለእያንዳንዱ ሎቶች 500 ብር (አምስት መቶ ብር) ብቻ በመከፈል ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ግዢ ዳይሬክቶሬት ብሎክ 7 መጥተው መግዛትና መውሰድ ይችላሉ።

5. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ሰነዱን ዋናውንና ኮፒውን በማሸግ ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በዚሁ ቀን ጨረታው ከቀኑ በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛው እለት 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በግልፅ ይከፈታል። ከተጠቀሰው ሰዓት ውጪ ዘግይቶ የሚመጣ ተወዳዳሪ ተቀባይነት የለውም።

6. በጨረታው አሸናፊው ጨረታውን አሸንፎ ውል እስኪፈራረም ድረስ ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ አይመለስለትም በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

7. ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8. አሸናፊው ተጫራች ተወዳድሮ ያሸነፈበት እቃ ኮሌጁ እቃ ግምጃ ቤት ድረስ በራሱ በትራንስፖርት ወጪ በማጓጓዝ ገቢ ማድረግ አለበት።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፉበት እቃ ዋጋ 1ዐ% የውል ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ ጀነራል ዊንጌት ፖሌ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም ማስያዝ አለባቸው።

በአ/ከ/ክ/ከ የወረዳ 10 ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

አድራሻ፡- ከመድኃኒዓለም መሰናዶ ት/ቤት ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ዊንጌት ቀለበት

ስልክ ቁጥር፡- 011 12 73 92 49 ሳይደርሱ ወይም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው።

ጀነራል ዊንጌት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ


Tender details

  • Deadline: 2026-09-30
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-09-30 12:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: General Wingate TVET College
  • Buyer address: ከመድኃኒዓለም መሰናዶ ት/ቤት ወደ አስኮ በሚወስደው መንገድ ዊንጌት ቀለበት መንገድ ሳይደርሱ ወይም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አጠገብ ነው
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: ለእያንዳንዱ ሎቶች 500 ብር (አምስት መቶ ብር)
  • Published on: Addis Zemen (Sep 18, 2026)
  • Posted at: 2026-09-18T09:13:36.000Z
  • Source: 2merkato
← Back to all tenders