Equipment and Accessories
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ የSubmersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/S/125/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለድሬዳዋ ፌዴራል ፖሊስ ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ዝርዝራቸው ከጨረታ ሰነዱ ጋር በተያያዘ የስራ ዝርዝር (Specification) መሰረት የ Submersible & Water Pump አቅርቦትና ገጠማ ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የስራ ዝርዝር |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን |
የጨረታ |
|
1 |
Supply install, test & Commission Submersible & Water Pump |
DCE/SF/125/2026
|
27/01/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 04:45
|
27/01/2019 ዓ.ም ከቀኑ 05፡00
|
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ፤ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የታደሰ ታክስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሠነዱ በተጠቀሰው ብዛት እና ስፔስፍኬሽን መሠረት መሆን ይኖርበታል።
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋናው መስሪያ ቤት የግዥ እና አቅርቦት አስተዳደር መምርያ መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ሠነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ መስከረም 27/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 04፡45 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው መስከረም 27/2019ዓ.ም ከጠዋቱ 05፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ቡድን ቢሮ ይከፈታል።
7. አንድ ተጫራች ለአንድ ዕቃ መወዳደር የሚችለው በአንድ ዓይነት ሞዴል/ብራንድ/ ብቻ ነው። በአማራጭ የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
8. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር ቁጥር 011 440-3434/33 ማዞሪያ 011 442-2270/71/72
www.dce-et.com /Email:- [email protected]
ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-10-07
- Bid closing time: 10:45
- Bid opening: 2026-10-07 11:00
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር)
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Sep 19, 2026)
- Posted at: 2026-09-19T08:07:46.000Z
- Source: 2merkato