Legal
ችዋችመን ብረታብረት እና ጠቅላላ ንግድ ሥራ አ.ማ. የገለልተኛ የሕግ አማካሪ ድርጅት ቅጥር ጨረታ ማስታወቂያ
Description
የገለልተኛ የሕግ አማካሪ ድርጅት ቅጥር ጨረታ ማስታወቂያ፤
ችዋችመን ብረታብረት እና ጠቅላላ ንግድ ሥራ አ.ማ. 1-ምድር- ቤት እና 5 ፎቅ(B+G+5) ያለው ሕንጻ እና ምድር (G+0) ሱቆችን አስገንብቶ በማከራየት ላይ ሲሆን 2-ምድር-ቤት እና 6 ፎቅ(2B+G+6) የመኖሪያ አፓርታማ በማስገንባት ላይ የሚገኝ አክሲዮን ማኅበር ነው:: ከመንግስት በወረደ አቅጣጫ መሠረት በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለመመዝገብ የአገበያየት አማካሪ (Iran action Advisor) አወዳድሮ በመቅጠር በምዝገባ ሂደት ሥራ ላይ ይገኛል።
ድርጅታችን በምዝገባ ሂደቱ ላይ ገለልተኛ የሕግ አማካሪ መቅጠር እንዳለበት ስለተረዳ ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ የሕግ ድርጅቶችን ለዚሁ ሥራ አወዳድሮ በጊዜያዊነት መቅጠር ይፈልጋል።
በመሆኑም መስፈርቱን የምታሟሉ የሕግ ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት ልምዳችሁን የያዘ ሞያዊ (Technical) እና ሒሳባዊ (Financial) ምክረ-ሀሳብ በታሸገ ፖስታ እንድታቀርቡ እንጋብዛለን።
አድራሻ፡ - +251935 – 40 93 05 አ.አ ኢትዮጵያ
Adress
Addis Ababa, Ethiopia
Tender details
- Deadline: 2026-09-25
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ተከታታይ 5 የሥራ ቀናት
- Bid opening: 2026-09-25 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Chewachmen Metal Trade S.C
- Published on: Reporter (Sep 20, 2026)
- Posted at: 2026-09-21T16:27:23.000Z
- Source: 2merkato